መስቀል ተ ሠላጢን

መስቀል እና ሠላጢን እንዴትና መቸ በማን እንደ ተጋጠሙ እቅጩን ማወቅ ያዳግታል። ሁለቱ የሚያበስሩት ፍልስፍና ግን የተድበሰበሰ ነገር የለውም። ወይ ሰላም ወይ ፀብ። ሰላም እና ፀብ። በሰላም ከመጣ አሳልመው፤ በፀብ ከመጣ ጎኑን ወግተህ ጣለው… ከጅምሩ የጠበኛና የጠርጣራ ሰው ሥራ ይመስላል፤ ጨርሶ…