የለቅሶ መስተንግዶ በመንግሥቱ ለማ

“ሬሳ ሲመጣ መንገድ ላይ እንዳትቆም” እያለች ዱሮ እናቴ ትከለክለኝ ስለነበር ለቀስተኞች ሲመጡ ባየሁ ቁጥር መንገድ ለቅቄ እሸሽ ነበር።በሰፈራችንም ሰው የሞተ እንደሆን ልጆች በዚያ አካባቢ ዝር እንዳንል እንከለከል ስለነበር የልቅሶ ትዕይንት ምን እንደሆን ብዙ ሳላውቅ አደግሁ። በቅርቡ ከአዲስ አበባ ውጪ ስሄድ…