ይድረስ ለዝጋቤር May 18, 2025 | by Mitiku Adisu | 0 ለኦቦ ቦጎሳ ቀኖ + ለአዴ ሶሬቲ መታሰቢያ ይሁን + ወንዙን ተሻግሮ ጉብታው ላይ ባለ ሣር ክዳን ቤት፤ ከአጠገቡ የተራበ ሕጻን ሆድ የምታክል ያጋደለች የእህል ጎተራ፤ ፈንጠር ብሎ ማማ፣ ማማው ላይ ከወጣህ የበቆሎ ማሣ ከዳር ዳር እንደ እጅህ መዳፍ ወለል ብሎ…