“ፕሮቴስታንታውያን በኢትዮጵያ ፖለቲካ”ን እንዳነበብኩት

የዮናስ ጎርፌን “ፕሮቴስታንታውያን በኢትዮጵያ ፖለቲካ” የተሰኘው መጽሃፍ አነበብኩት።ሃይማኖት፣ ሃይማኖተኞችና ታሪክን ይሄሳል።’ተከድነው ይብሰሉ’ የተባሉ ሃይማኖታዊ ጉዳዮችን መጽሃፉ በድፍረት ቃኝቷል።ፈረንጅ ሚሽነሪዎች፣ የፕሮቴስታንት እምነትን በኢትዮጵያ ያስፋፉበት መንገድ በመጽሃፉ በስሱም ቢሆን ተዳስሷል።በሚሽነሪዎች ተኮትኩተው ያደጉት ኢትዮጵያውያን ወጣቶች፣ በ1966ቱ አብዮት ሰሞንና ማግስት ያመረሩ “የዘውጌ ብሄርተኛ” ለምን ሆኑ? ሲል ይጠይቃል።ባለፉት ስድስት ዓመታት ፕሮቴስታውያን እያደረጉት…