የዛሬው መልዕክተ ቅዳሜ እንደ ሌላው ጊዜ ብዙ አስቤበት የመረጥኩት ርዕስ ሳይሆን የበይነ መረቡ አየር አስገድዶኝ ያረፍኩበት ርዕሰ ጉዳይ መሆኑን ከወዲሁ እየጠቆምኩ ወደ ፍሬ ጉዳዮ ልግባ፡፡ እንደ አገር ጸረ እውቀት፣ ጸረ ትምህርት፣ ጸረ ግንዛቤ፣ ጸረ ሳይንስ በሌላ አገላለጽ ድንቁርና፣ አላዋቂነት፣ ይሉኝታ…
እንደምን ከርማችኋል የመልዕክተ ቅዳሜ ታዳሚዎች? ላለፉት ሁለት ሳምንታት ስብሰከሰክበት በቆየሁት ርዕስ ላይ ለማተኮር ወደድኩ፡፡ ለምን ጭካኔያችን በዚህ ልክ በረታ? ለምን እርስ በርስ መጠፋፋትን መረጥን? ለምን በበደሎቻችን ክብደት መለካካትን መረጥን? ለምን የአንዳችን ስቃይ የሌላችን የፖለቲካ ግብ ማቀንቀኛና ማሳለጫ ሆነ? ለምን እንዲህ…
በዛሬ ሳምንቱ የመልዕክተ ቅዳሜ ዳሰሳ የአብላጫውን ቁጥር ስለያዘውና ዝምታን ብቸኛና የተሻለ ምርጫው አድርጎ በገዛ አገሩ የዜግነትና የሰውነት ክብር ተነፍጎት የራሱን እና የልጆቹን እጣፈንታ ለጥቂት ደፋርና ውል አልቦ ልሂቃን እርግፍ አድርጎ ትቶ የታዛቢነትን፣ የተመልካችነትን፣ የተጉረምራሚና መስሎ አዳሪነትን መገለጫ ስላደረገው የአገራችን ሰፊ…
የጠቅላይ ሚኒስትሩን የዛሬ የፓርላማ ንግግርን ጊዜ ወስጄ፣ አንዳንዱንም እርግጠኛ ለመሆን ደግሜ ሰማሁት፡፡ ጠቅለል ሲደረግ ‘የለየልኝ አምባገነን መሆኔን የኢትዮጵያ ሕዝብ፣ ጎረቤት አገሮችና የቀረው አለም ይወቅልኝ’ የሚል እንድምታ ያለው የጸብ እወጃ የጀመረ ንግግር ነው፡፡ ጠቅላዩ ሦስቱንም የአንባገነን ሥርአቶች ባህሪያት፤ (benevolent, military and…
በትላንትናው የመንግስት ዜና እወጃ የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽነሩ በሰጡት መግለጫ በአዲስ አበባ ከተማ ውስጥ ማህበራዊ ድህረ-ገጾችን በመጠቀም ለአመጽ ቅስቀሳ የሚያደርኩ አካላትን አድኖ ለመያዝ የተጠናከረ የጅምላ ፍተሻና የእጅ ስልክ ብርበራ እንደሚያደርግ ዛቻና ማስፈራሪያዎች የተቀላቀለበት መግለጫ ሰጥቷል። በመጀመሪያ ይህ ዜጎችን በየመንገዱ ድንገት አስገድዶ…
ሹም ማቅበጥ፣ ማሞሰን፣ ማባለግ፣ ሕዝብ አናት ላይ ወጥተው ፊጢጥ እንዲሉ፣ ከሕግ እና ከሀገር በላይ እራሳቸውን እንዲቆጥሩ እና ቶሎ እንዲታበዩ ማድረግ፣ ትክክለኛውን መስመር ማሳት እናውቅበታለን። የኢትዬጲያ ሕዝብ በዚህ ሁሉ የረዥም ዘመን ታሪኩ ከተሳኑት ነገሮች አንዱ ሥልጣንን መግራትና ማረቅ ነው። ሥልጣንን እና…
ከልክ ያለፈም ትዕግስት፤ ከልክ ያለፈም የኃይል አጠቃቀም መንግስታዊ ባህሪዎች አይደሉም። አንዱ የመንፈሳዊ ሰው ሌላው የአፋኝ ቡድን ባህሪዎች ናቸው። ቀኝህን ሲመታህ ግራህን ስጠው የሚለው መንፈሳዊ አስተምህሮት የመንግስት ባህሪ አይደለም፤ ሊሆንም አይችልም። መንግስት ቀኝ ሲመታ መቺውን በሕግ ጥላስር አውሎ ተጠያቂ ያደርጋል እንጂ…
ሰውየው አጥብቆ የሚፈልጋትን የልብ ወዳጁን እሱ በፈለጋት ጊዜ ፈልጎም አያገኛትም፤ እሷ በፈለገችው ጊዜ ደግሞ ድንገት ከች ትላለች። በዚህ የተበሳጨው አፍቃሪ ታዲያ እንዲ ብሎ ገጠመ ይባላል፤ አንቺን ሲልሽ ሲልሽ ትመጫለሽ በእግርሽ፣ እኔን ሲለኝ ሲለኝ የትም አላገኝሽ።በአገሪቱ የሕግ የበላይነት ከጠፋ ከሁለት አመታት…
አዲስ አበባ ብዙ ሥር የሰደዱ እና ውስብስብ ችግሮችን በጉያዋ የያዘች ጉደኛ ከተማ ነች። ልክ እንደ ከተማዋም አዲስ አበቤዎችም እንዲሁ ከዳቦ አንስቶ እጅግ ብዙ እና ውስብስብ የመብት እና የጥቅም ጥያቄዎች እንዳረገዙ ከዚህ ሁሉ ጭንቅ የሚገላግላቸው አስተዳደር ሲናፍቁ ዘመናት ተቆጥረዋል። ይህ ችግር…
ትላንት በተወካዮች ምክር ቤት መደበኛ ስብሰባ ላይ ተገኘትው ለምክር ቤቱ አባላት ጥያቄዎች ምላሽ ሲሰጡ የነበሩት ዶ/ር አብይ ለበርካታ ጥያቄዎች አግባብነት ያለው ምላሽ ቢሰጡም በሁለት ጉዳዮች ግን ሲፎርሹ ታዝቤያለሁ። አንደኛው የታፈኑትን ሴት ተማሪዎች በተመለከተ የተናገሩት ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ የአምነስቲ ኢንተርናሽናልን መግለጫ…