የከረመ ፈረስ

በማር መጥተውባት፣ መሯት። ንቢት ንዴት አሳብዷት ቀፎዋን ጥላ ቱር አለች። በመስኮት ገብታ የአቶቡሱን ሾፌር አፍንጫው ላይ ነደፈችው። ሾፌር አፍንጫው ከምኔው ረዛዝሞ ዐይኑን ሲያጥበረብረው። መርዙ እ ንደ እልህ እንደ ቂም እንደ ጥላቻ እንደ አጋንንት ሳቅ ተሠራጭቶ እንደ እብድ እንደ ሰካራም ሲያደርገው።…