እስራኤል በኢራን የኒውክሌር ሥፍራዎች እና የጦር አዛዦቿ ላይ በማነጣጠር የፈፀመችው ከፍተኛ ጥቃት በመካከለኛዉ ምሥራቅ ትልቅ ውጥረትን ፈጥሮል፤ የነዳጅ ዘይት ዋጋም እንዲሻቅብ አድርጐል።ብዙዎች ቀጣዩ ምንድነው የሚል ጥያቄ በማንሳት ላይ ናቸው።
ኢራን መቼና የት ነው ያፀፋ ምላሽ የምትሰጠው?
የእስራኤን ጥቃት ተከትሎ ዓርብ ጠዋት ላይ ኢራን በእስራኤል ላይ መጠነ ሰፊ የድሮን ጥቃቶችን በመፈጸም ምላሽ ሰጥታለች።ሁሉም ግን እንዲከሽፉ ተደርጏል ሲል የእስራኤል ጦር አስታውቋል። አርብ ምሽት ላይ “እውነተኛ ቃል ኪዳን 3” ብሎ በሚጠራ ዘመቻ ኢራን በእስራኤል ላይ በርካታ ባሊስቲክ ሚሳይሎችን አስወንጭፋለች።ነዋሪዎች በቦምብ መጠለያ አካባቢ እንዲሆኑ የእስራኤል ሠራዊት ሲመክር፣ የአደጋ ማስጠንቀቂያ ጥሪ በመላ ሃገሪቱ ተሰምቷል።
የብሪታንያውያኑ ዕለታዊ ጋዜጣ ፋይናንሻል ታይምስ እንደሚለው፣ ኢራን መደበኛ ባልሆነ ውጊያ ላይ ልትሳተፍ ትችላለች። ከዚህ ቀደም ቴራን ጥቃት ከተሰነዘረባት የሆርሙዝን የባሕር ወሽመጥ እንደምትዘጋ ወይም እንደምታናጋው ዝታ ነበር።ኢራን እና ባህረ ሰላጤ የሚለያዩበት ወሽመጥ ሲሆን 30 በመቶ የሚሆነው ወደ ውጭ ሀገራት የሚላከው የነዳጅ ዘይት የሚያልፈው በዚህ መንገድ ነው።
ከተወሰኑ አመታት በፊት ኢራን በሳዑዲ አረቢያ የነዳጅ ማቀነባበሪያ ተቋማትን በማጥቃት ከባድ ጉዳት አድርሳለች። ባለፉት 18 ወራት በእጅጉ ቢዳከሙም፣ የሊባኖሱ ሔዝቦላህ፣ የየመኑ ሁቲ ቡድኖች በእስራኤል ላይ አሁንም ጥቃቶችን መፈፀም ይችላሉ።
ኢራን ከአሜሪካና ጋር የምታደርገው የኑክሌር ውይይት ይቀጥል ይሆን?
በአሜሪካ እና በኢራን መካከል የተጀመረው ድርድር ነገ እሁድ ይቀጥላል ተብሎ ነበር።የሁለቱ ወገኖች ድርድር ይቀጥላል አይቀጥልም የሚለው ለጊዜው ግልጽ አይደለም።
አሜሪካ በጥቃቶቹ እንዳልተሳተፈች የገለፀች ሲሆን ኢራን ግን አሜሪካ ደግፋለች ስትል ከሳለች። የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ትራምፕ ዓርብ ጠዋት ላይ ኢራን በኒውክሊየር ፕሮግራሟ ላይ ከስምምነት ላይ ካልደረሰች ከአሁኑ የከፋ ከባድ ጥቃት ይገጥማታል ሲሉ አስጠንቅቀዋል።ዶናልድ ጥሩምፕ ቴህራን ስምምነት ላይ ለመድረስ ብዙ አጋጣሚዎች እንደተሠጧት ከገለፁ በኅላ ‹‹ኢራን ከመዘግየቱ በፊት ስምምነት ማድረግ አለባት፤›› በማለት ተናግረዋል።
የእስራኤል ዋና አላማ ምንድን ነው?
የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንጃሚን ኔታንያሁ ጥቃቶቹ የኢራንን የኒውክሌር መሠረተ ልማቶችንና የባሊስቲክ ሚሳኤል ማምረቻ ተቋማትን ለማውደም የተፈጸሙ እንደሆኑ ተናግረዋል። ዘመቻው በእስራኤልና በእስራኤላውያን ሕልውና ላይ የተጋረጠው ስጋት እስከሚወገድ ድረስ እንደሚቀጥልም ቃል ገብተዋል። እስራኤል ባለፈው ዓመት በሊባኖሱ ታጣቂ ቡድን ሄዝቦላህ ላይ ያካሄደችው ዘመቻ አብዛኛዎቹ ከፍተኛ አመራሮችን የግድያ ወንጀል ተጠናቋል። አንዱ ጥያቄ የእስራኤል ዋነኛ ዓላማ የኢራንን የኒውክሌር መርሀ ግብር ማጥቃት ብቻ ነው ወይስ የኢራንን አገዛዝ መገርሰስ የሚለው ነው።
ዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ተፅዕኖ ማሣረፍ ይችላልን?
ነገ እሁድ ትራምፕን ጨምሮ የቡድን ሰባት (ጂ7) መሪዎች በካናዳ ይሰበሰባሉ። የመወያያ ዋና ርዕሳቸውም እስራኤልና ኢራን እንደሚሆኑ ይጠበቃል። የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዚደንት በእስራኤል ላይ ከፍተኛ ተፅዕኖ ማሣደር ይችላሉ። ይሁንና፣ በአሁኑ ወቅት ትራምፕ ፣ኔታንያሁን ለመግራት ፍላጐት እንዳላቸው የሚጠቁም ምንም ነገር የለም።