የፓርላማው ውሎ፤ ዛቻ፣ ውሸት፣ ስድብ እና ትምክህት

የጠቅላይ ሚኒስትሩን የዛሬ የፓርላማ ንግግርን ጊዜ ወስጄ፣ አንዳንዱንም እርግጠኛ ለመሆን ደግሜ ሰማሁት፡፡ ጠቅለል ሲደረግ ‘የለየልኝ አምባገነን መሆኔን የኢትዮጵያ ሕዝብ፣ ጎረቤት አገሮችና የቀረው አለም ይወቅልኝ’ የሚል እንድምታ ያለው የጸብ እወጃ የጀመረ ንግግር ነው፡፡ ጠቅላዩ ሦስቱንም የአንባገነን ሥርአቶች ባህሪያት፤ (benevolent, military and…