በአንዳንዶች የኢትዮጵያ የባህል ሙዚቃ አባት የሚል የቁልምጫ ሥም የተሰጠው እውቁ ሙዚቃ ሰው ነፍሰሄር ተስፋዬ ለማ “የኢትዮጵያ ሙዚቃ ታሪክ ክ 1889-1983 ዓ.ም” በተባለው መፅሐፉ ላይ በዚህ ሳምንት ስላረፈው በረከት መንግሥተአብ ይህንን ፅፎ ነበር።
በረከት መንግሥተአብ ከ1948 ዓ.ም. ገደማ ጀምሮ በቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ቴያትር ያገለገለ ዝነኛ ባለሙያ ነው:: በዚያን ዘመን የበረከት ሙዚቃዎች እጅግ ተወዳጅ ስለ ነበሩ ለቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ ቴያትር የባህል ክፍል ልዩ ድምቀት ሰጥቶ ነበር። በረከት ረጋ ያለና ከሰዎች ተግባቢ ሲሆን፣ ምርጥ የትግርኛ ዘፈኖቹን አጣፍጦ በመጫወት በዘመኑ ተወዳዳሪ አልነበረውም። በረከት ከሙዚቃ ሙያው በተጨማሪ መርካቶ በሀብተ ጊዮርጊስ ድልድይ አካባቢ የሙዚቃ መሸጫ ሱቅም ነበረው። ከአሥራ አምስት ዓመታት በፊት ዋሸንግተን ዲሲ ውስጥ አግኝቼው ስንጨዋወት ቀድሞ ኢትዮጵያ ውስጥ ያሳለፈው ጊዜ ግሩም እንደ ነበር አስታውሶኛል። ደርግ ሲመጣ ግን ሽብርና ግፍ በመከተሉ ወደ ትውልድ ሀገሩ ወደ ኤርትራ በመሄድ ከሽምቅ ተዋጊዎች ጋር መቀላቀሉንና በሙያው በረከት መንግሥተአብ ማገልገሉን አጫውቶኛል፡፡ በአሁኑ ወቅት አልፎ አልፎ ወደ መካከለኛው ምሥራቅ፣ አውሮፓና አሜሪካ ጐራ እያለ ከመጫወቱ በስተቀር በሙያው ለረጅም ጊዜ በማገልገሉ ዕረፍት በማድረግ ላይ መሆኑን ገልጾልኛል።
“የኢትዮጵያ የባህል ሙዚቃ አባት” የተባለው በ ትግርኛ ስለ ዘፈነ ከሆነ ትልቅ ስህተት ነው። ለዚያውም በቁዋሚነት “ኤርትራዊ ነኝ” እያለ!
ለነፍሰሄር ተስፋዬ ለማ የተሠጠ ስም ነው።
ይቅርታ።
አከታትዬ መንግሥተአብን አግንነው የዘገቡ ሁለት ሦስት ድረገፆችን እየተመለከትኩ ነበር። የባህል ሙዚቃችንን በተመለከተ አቶ ተስፋዬ ለማን የሚተካከል የለም። ተጨማሪ ምስክር ካስፈለገ፣ አሜሪካዊውን፣ የጌታ መሳይ አበበን ወዳጅ፣ ቻርለስ ሰተንን መጥራት ይቻላል፤ ከቦስተን እስከ ዲሲ “ሸጊቱ ሸጊቱ”ን በማሲንቆው ሲዘፍን።