ከሃረር ባቢሌ

በቅርቡ ወደ ኢትዮጲያ ለአጭር ጊዜ በሄድንበት ወቅት ሃረር እና ባቢሌንን የመጐብኘት እድል አግኝተን ነበር። በብዙ የአገሪቱ ቦታዎች ላይ የፀጥታ ችግር እንዳለ ብናውቅሞ፤ እዚያ አካባቢ ብዙም ስጋት እንደሌለ ወዳጆቻችን ነግረውን ስለነበር ነው ወደዚያ ያቀናንው።እንደተነገረንም የሐረር ጉብኝታችንን ያከናወንው ያለምንም ፀጥታ ችግር ነበር።…