በጅቡቲ የባህር ዳርቻ የስደተኛ ጀልባ ተገልብጣ ቢያንስ 109 ሰዎች ህይወታቸውን ሲያጡ ብዙ ሰዎች ጠፍተዋል ሲሉ ባለስልጣናት ተናግረዋል። ጀልባዎ ከመስመጧ በፊት 350 ሰዎችን አሳፍራ ከጅቡቲ ወደ የመን በመጓዝ ላይ እንደነበረች የአለም አቀፍ የስደተኞች ድርጅት (አይኦኤም) አስታውቋል። የባህር ጠረፍ ጠባቂ “እስካሁን ድረስ 116 ግለሰቦች የጠፉ ሲሆን የማፈላለጉ ስራም ያለ እረፍት ቀጥሏል” ብለዋል።ጀልባዎ የሰመጠችው በጅቡቲ ከተማ ኦቦክ ክልል አቅራቢያ ካለ የባህር ዳርቻ ላይ መሆኑን የባህር ዳርቻ ጥበቃው ጨምረው መናገራቸው ተዘግቧል፡፡ከተገኙት 109 አስከሬኖች መካከል 52 ወንዶች፣ 42 ሴቶች እና 15 ሕፃናት ይገኙበታል። ከ80 በላይ ሰዎች በሕይወት የተረፉ ሲሆን፣ ሁሉም የኢትዮጵያ ዜጎች መሆናቸውን ተገልጿል።
አደጋው የደረሰበት አካባቢ ወደ አረብ አገራት የሚደረጉ ሕገ-ወጥ የባህር ላይ ጉዞዎች ዋነኛ መነሻ በመሆኑ ከዚህ ቀደም መሰል የጀልባ መስመጥ አደጋዎችን አስተናግዷል። በጅቡቲ የዓለም አቀፉ የስደተኞች ድርጅት ኃላፊ አሌክሳንድር ኳሳክ “የጠፉትን ለማግኘት እና የተረፉትን ደህንነታቸውን ለማረጋገጥ ቁርጠኞች ነን” ብለዋል።
በጅቡቲ የባህር ዳርቻ ጀልባ ሰጥማ 109 ሰዎች ሲሞቱ 116 ሰዎች ጠፍተዋል ተባለ፡፡