እንዳሰብነው አልሆነም፤ እንደ ፈራነው ሆነ

ሰው ከሞላ ጎደል የግንኙነቶቹ ውጤት ነው። ከወላጅ ቤት ትምህርት ቤት። ከደደቢት ከአሲምባ ምንሊክ ቤት። ከዳንስ ቤት ጸሎት ቤት። ከእሥር ቤት ፍርድ ቤት፤ ወደ ስደት ወደ አገር ቤት። የውጣ ውረዱ ተፅእኖ ቀላል አይደለም። መንገዱ ረጂም ዘወርዋራ ነው። ለያንዳንዱ ተሸክሞት የሚዞረው ኮሮጆ…