በሙስና የተጨማለቁት ዶናልድ ትራምፕ እና ቤተሰቦቻቸው

በሙስና የተጨማለቁት ዶናልድ ትራምፕ እና ቤተሰቦቻቸው

መስከረም 2025 ላይ ዮናይትድ ስቴትስን የጐበኙት የካዛኪስታን መሪ ከዶናልድ ትራምፕ ጋር አንድ ውልን ተፈራረሙ።እንደ ኒውዮርክ ታይምስ ዘገባ፣ ውሉ የሚያካትተው የጦር መሣሪያ፣ ኤሌክትሮኒክ ቺፖች እና ሌሎች ወሳኝ ምርቶች ለማምረት አስፈላጊ የሆነውን እና በካዛኪስታን በብዛት የሚገኘውን ቱንጂሳተን የተባለ ማዕድን ለማውጣት ለአሜሪካ ኩባንያ ካዝ ሪሶርስስ ፈቃድ ስለመስጠት ነው።በምላሹም ዋይት ሀውስ ለካዝ ሪሶርስስ 1.6 ቢሊዮን ዶላር የመንግሥት ፋይናንስ አፀደቀ።ድርድሩ በመካሄድ ላይ እንዳለ፣ በትራምፕ ልጆች፣ ኤሪክ ትራምፕ እና ዶናልድ ትራምፕ ጁኒየር ባለቤትነት የተያዘው ዶሚናሪ ሴኩሪቲስ (Dominari Securities) የተባለ ድርጅት፣ ከዚህ የካዛኪስታን የማዕድን ፕሮጀክት ጋር በተያያዘ 20 በመቶ ድርሻ ገዛ።

ትራምፕ አሜሪካ ወደነበረችበት ታላቅነት እመልሳታለሁ የሚል ቃል ኪዳን በመግባት ነበር ወደ ሥልጣን የመጡት።እስካሁን ባለው ሁኔታ የተሳካላቸው ቢኖር ራሳቸውን እና ልጆቻቸውን ማበልፀግ ነው። “ትራምፕ ወደ ሥልጣን ከመጡ ጀምሮ ከዚህ በፊት ታይቶ በማይታወቅ ሁኔታ ሥልጣናቸውን በመጠቀም ራሳቸውን አበልፅገዋል” ይላሉ በኦባማና በቡሽ አስተዳደር ዘመን የሥነ-ምግባር ጉዳዮችን ይከታተሉ የነበሩት ጠበቆች ኖርም ኤይሰን እና ሪቻርድ ፔይንተር። 927 ገጽ ያለው የዓመታዊ ገቢና ወጪዎች ሪፖርታቸው እንዳመለከተው፥ ዶናልድ ትራምፕ በ2025 ዓ.ም 2,2 ቢሊዮን ዶላር በላይ አግኝተዋል። ይህ የትራምፕ ገቢ ከቀደመው ዓመት ማለትም እአአ በ2024 ከነበረው አራት እጥፍ ያህል የላቀ ነው። ለዚህም ነው የሥነ-ምግባር ባለሙያዎች የጥቅም ግጭት እንዳለ ማስጠንቀቂያ እያሰሙ ያለው። “ለምን ትርፍ እያገኘሁ እንደሆነ ታውቃላችሁ? የአክሲዮን ገበያው እየጨመረ ስለሆነ” ሲሉ ትራምፕ ተናግረዋል።

ግን ምክንያቱ እርሱ ብቻ አልነበረም።ከዚህ እጅግ ከፍተኛ ገቢ ከግማሽ በላይ የሆነው፣ 1.4 ቢሊዮን ዶላር የተገኘው በክሪፕቶከረንሲ ባደረጉት የንግድ እንቅስቃሴ ነው።ያም ፕሬዝዳንቱ ወደ ዋይት ሃውስ ከተመለሱ በኋላ ለክሪፕቶከረንሲ ኢንደስትሪ ተስማሚ የሆነ አሰራር ይዘው በመምጣት ለግላቸው ከፍተኛ ጥቅም ለማግኘት ስላመቻቹት ነው። ክሪፕቶ የባንክ ጣልቃ ገብነት ሳያስፈልገው ደኅንነቱ የተጠበቀ ቴክኖሎጂን የሚጠቀም ዲጂታል የገንዘብ ዓይነት ሲሆን የሜም ኮይን የትራምፕ ዋነኛ የገቢ ምንጭ ሆኗል። የትራምፕ ምሥል ካለው ኮይን “$TRUMP” ክፍያ፥ፕሬዝዳንቱ ወደ 635 ሚሊዮን ዶላር አግኝተዋል።ከዚህም በተጨማሪ በልጆቻቸው ከተመሰረተው ‘ዎርልድ ሊበርቲ ፋይናንሻል’ ከተባለው የክሪፕቶከረንሲ ድርጅት ከ800 ሚሊዮን ዶላር በላይ ገቢ አግኝተዋል።ከዚህ ገቢ ውስጥ የተወሰነው የተገኘው በሚስጥር በተደረገ ግዢ ሲሆን የተባበሩት የአረብ ኤሚሬቶች 49 በመቶ ድርሻ ገዝታለች

የትራምፕ ድርጅት (The Trump Organization) በውጭ አገራት ሪልስቴት ፕሮጀክቶቹ ገቢ ማግኘቱን እንደቀጠለ ነው።በኳታር እና ሳዑዲ አረቢያ የቅንጦት የጎልፍ ሪዞርቶችን ለመገንባት ስምምነት ተፈራርሟል፤14 ሚሊዮን ዶላር የሚያስገኝ።ትራምፕ በቬትናም የጎልፍ መጫወቻ ስፍራ ለመገንባት ሲወስኑ፥ ለመገንባት የሚያስፈልገውን ፈቃድ በሚገርም ፍጥነት አግኝተዋል።በዚህ ወቅት፥ ሃኖይ ቀረጥ እንዲቀነስላት ከአሜሪካ ጋር ድርድር ላይ ነበረች።ከዚህም በተጨማሪ ፕሬዚደንቱ ከተለያዩ የሕግ እርምጃዎች 80 ሚሊዮን ዶላሮች አግኝተዋል፤ ከኤቢሲ እና ከሜታ ያገኙትን ጨምሮ።በእነርሱ ላይ ፕሬዘዳንቱ ያቀረቡት ክስ ውድቅ እንዲሆንላቸው እና ፈቃዳቸው ሊሠረዝ የሚችልበትን አደጋ ለለማስቀረት በመፈለግ የከፈሉት ክፍያ።

ፕሬዚዳንት ትራምፕ በ2026 የመጀመሪያው ሩብ ዓመት ውስጥ በስማቸው የተፈጸሙ በመቶ ሚሊዮኖች ዶላር የሚያወጡ ግብይቶችን አድርገዋል፤ ወደ 3,642 የሚደርሱ ግብይቶችን። ትራምፕ ከ1 ሚሊዮን ዶላር በላይ በማውጣት የዴል (Dell) ኩባንያ አክሲዮን ገዝተዋል።ይህ የሆነው ኩባንያው የ9.7 ቢሊዮን ዶላር ውል ከፔንታጎን ከማግኘቱ ጥቂት ወራት በፊት ነው። “የዴል ኮምፒውተርን ግዙ” ሲሉ ትራምፕ ለድርጅቱ ማስታወቂያ ሠርተዋል

ዶናልድ ትራምፕ በአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ (AI) ቺፕ ኩባንያው ኒቪዲያ (Nvidia) ላይ ኢንቨስት አድርገዋል። መንግሥታቸው ድርጅቱ ቻይና ውስጥ ቺፖችን እንዲሸጥ ከመፍቀዱ ጥቂት ጊዜ በፊት ፤ወዲያውኑ የኒቪዲያ አክሲዮን ዋጋም በከፍተኛ ሁኔታ ጨመረ።

ትራምፕ በማጭበርበር ወንጀል ለተከሰሱ በመቶዎች ለሚቆጠሩ ሰዎችን ምህረትን አድርገዋል። እነዚህ ይቅርታ የተደረገላቸው ግለሰቦች ለትራምፕ የምርጫ ዘመቻ ገንዘብ ሰጥተዋል።የአማዞን መሥራች ጄፍ ቤዞስ ለትራምፕ በዓለ ሲመት 1 ሚሊዮን ዶላር ሰጥተዋል።እንደዚሁም፥ የቀዳማዊት እመቤት ሜላኒያ ትራምፕን ታሪክ የሚያወሳ ዘጋቢ ፊልም የማሰራጨትና የመጠቀም መብት ለማግኘት 40 ሚሊዮን ዶላር ከፍለዋል።ይህም ለጄፍ ቤዞስ ጥቅም አስገኝቶላቸዋል። ብሉ ኦሪጂን የተሰኘው የጠፈር ኩባንያቸው ከፌዴራል መንግሥት ከ1 ቢሊዮን ዶላር በላይ የሚያወጡ ኮንትራቶችን ለማግኘት ችሏል።

Share this post

Post Comment