የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ፣ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ (ኤአይ) የሰው ልጅን ከምድረገፅ ሊያጠፋ ይችላል የሚለውን ስጋት አጣጥለውታል። ከዛ ይልቅ፣ አገራቸው በኤአይ ውድድር በቻይና የመበለጥ አደጋ እንደሚያሳስባቸው ተናግረዋል።ኤአይ የሰው ልጅን ያጠፈዋል ብለው ይሰጉ እንደሆነ ጥያቄ ሲቀርብላቸው፣ ትራምፕ፣ «አይ፣ ምንም አይነት ስጋት የለኝም» ሲሉ መልሰዋል። “ስጋቴ በኤአይ ማሸነፍ ካልቻልን፣ በጣም አስቸጋሪ በሆነ ሁኔታ ውስጥ እንገባለን” ሲሉ ፕሬዚዳንቱ ሐሙስ ዕለት ለጋዜጠኞች ተናግረዋል።“በአሁኑ ጊዜ ቻይናን በበኤአይ ዘርፍ በጥሩ ልዩነት እየመራናት ነው፤ በአንድ ዓመት ያህል በልጠናታል፣ ይህም ጥሩ በሚባል ደረጃ ነው” ብለዋል።
አሜሪካ እና ቻይና በሰው ሰራሽ ልሕቀት ቴክኖሎጂ የበላይነት ለመያዝ በከፍተኛ ፉክክር ላይ ናቸው፤ የቻይና የኤአይ ሞዴሎች በመሻሻላቸው እና በዓለም ዙሪያ ተጠቃሚያቸው እየጨመረ በመምጣቱ በሁለቱ ሀገራት መካከል ያለው ውጥረት እያየለ ነው። ለትራምፕ ይህ ጥያቄ የቀረበላቸው ሰሞኑን አንድ የአንትሮፒክ ሠራተኛ የነበረ ሰው በፍጥነት እየተመነጠቀ ያለው ይህ ቴክኖሎጂ በአስር አመት ጊዜ ውስጥ ከምድረገፅ ሊያጠፉን ይችላል ብሎ ከተናገረ በሗላ ነው።
የአንትሮፒካ ተመራማሪው ጃኮብ ኮክሰን ማክሰኞ ዕለት ከኩባንያው መልቀቁን በማስመልከት በሠጠው ቃለመጠይቅ አንትሮፒክ እና ተፎካካሪው ኦፐንአይ “በሕይወታችን ላይ ቁማር እየተጫወቱ ነው” ሲል ተናግሯል።
በተጨማሪም፣ ኤአይን በማዳበር ላይ ባለሙያዎች ይህ ቴክኖሎጂ “በዚህ አስርት ዓመት መጨረሻ ላይ ሁላችንንም ሊገድል ይችላል” ብለው እንደሚያምኑ ጨምሮ ተናግሯል። ከዚያ ወዲህም ሌሎች የAI ሰራተኞች በሃሳቡ እንደሚስማሙ ገልፀዋል።
የአንትሮፒክ የደህንነት ኃላፊ ኢቫን ሁቢንገር በኤክስ ገፁ ላይ ባወጣው ፅሑፍ፦ “ኤአይ ሁሉንም ሰዎች ሊገድል እንደሚችል በ ትክክል እናምናለን” ሲል ጽፏል። በእርሱ ግምት ይህ አደጋ በሚቀጥሉት አሥር ዓመታት ውስጥ የመድረስ ዕድሉ “ከ10% በላይ” እንደሆነ ገልጿል።