ሐብል፣ አምባር፣ ጒትቻ ስልክ እና ጸሎት

እንደ ዘመኑ ሰው ስልኩም ወሬኛ ወረተኛ ሆነ። የፈረንጅ ስልክ አገራችን ከመግባቱ በፊት ሰው ከወዲያ ወዲህ ተጠራርቶ መጫጯህ ወጉ ነበረ፦ “ወይፈኑ ከጊደሮችህ ጋር መጥቶ ይሆን? …ኡዉይ! … ጠበል ቅመሱ! ቡና ጠጡ! …ኡዉይ! … ወንዙን እንደ ተሻገራችሁ፣ ከጒብታው ላይ ኢየሱስ ይታያችኋል፤ በስተቀኝ…