የዓለም ዋንጫ እና የአባቢዮን ትዝታዬ June 14, 2026 | by ደረጀ ትዕዛዙ ስመኝ | 0 የዓለም ዋንጫ ሰሞን ለእኛ ሰፈር ልጆች ደስ የሚል ረጅም ዓመት በዓል ነበር። ቴሌቪዢን ብርቅ በሆነበት፣ የጣሪያ ላይ አንቴና የሀብታም ቤት መለያ በሆነበት በዚያ ዘመን፤ የዓለም ዋንጫን ለማየት የማይጓጓ የለም። እንዲህ አይነት ቤቶችን ደጅ መጥናት ግድ ይለን ነበር። እንቡሹ ጓደኛችን ነው፤…