ሶማሊያ የኤምሬትስ አምባሳደር በ72 ሰዓታት ውስጥ ሞቃዲሾን ለቀው እንዲወጡ አዘዘች

ሶማሊያ የኤምሬትስ አምባሳደር በ72 ሰዓታት ውስጥ ሞቃዲሾን ለቀው እንዲወጡ አዘዘች

ሶማሊያ የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች አምባሳደር በ72 ሰዓታት ውስጥ ሞቃዲሾን ለቀው እንዲወጡ አዘዘች።የሶማሊያ የማስተወቂያ ሚኒስትር አብዲፈታህ ካሲም ሞሃሙድ የኤምሬትስ አምባሳደር ሶማሊያን ለቀው እንዲወጡ የ72 ሰዓት ግዜ መሰጠቱን አስታውቀዋል።

በዚህ ሳምንት የሶማሊያ ፕሬዝዳንት ሐሰን ሼክ ሞሐሙድ፣ ዩናይትድ አረብ ኤምሬትስ በአገራቸው ውስጣዊ ጉዳዮች ጣልቃ እየገባች፣ የፌዴራል መንግሥቱን በመቃወም የታጠቁ ሀይሎችን እየደገፈች እና የሶማሊያን አንድነት እያዳከመች ነው ሲሉ ከሰዋል።

የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ ከሶስት የሶማሌ ክልሎች ሶማሌላንድ፤ ፑንትላንድ እና ጁባላንድጋር የቅርብ የንግድና የፀጥታ ግንኙነት አላት።

ነገር ግን የሶማሊላንድ፣ የፑንትላንድ እና የጁባላንድ ባለሥልጣናት ሞቃዲሾ ከአረብ ኤምሬትስ ጋር ያሉ ስምምነቶችን ለመሰረዝ የወሰደችውን ውሳኔ ውድቅ በማድረግ የራሳቸውን መንገድ እንደሚከተሉ አስታውቀዋል።

Share this post

Post Comment