ሐዘንሽ አመመኝ- ደበበ ሰይፉ

ውል አልነበረንም የፍቅር ቀጠሮቃልም አላኖርንም በወግ ተቀምሮ፤እኔ አንቺን እንዳላይአንቺ እኔን እንዳታይ አምባችን ተቃጽሮዕጣችን ተካሮ፤ቀለምሽ ከዐይኔ አሻራሽ ከጣቴ ባይጠፋ ተማትሮ(እትብት እምብርት ሁኖ እንዲኖር ደድሮ) ይኸው አካሄደን በድንገት ዘንድሮ። የገጽሽ ብርሃን ቢጠይም ፀዳሉ ድምፅሽ ቢቀጥንብኝ ቢሠልብኝ ቃሉወዘናሽ ቢማስን ዛሬ ያለውሉበእጆችሽ ጨበጠኝ ሐዘንሽ…