“ትራምፕ ኢራን በፍጥነት እጅ አለመስጠቷ መገረምን ፈጥሮበታል።”ክርስቲያን አማንፑር

“ትራምፕ ኢራን በፍጥነት እጅ አለመስጠቷ መገረምን ፈጥሮበታል።”ክርስቲያን አማንፑር

የኢራን ዝርያ ያላት አንጋፋዋ የሲኤንኤን ጋዜጠኛ ክርስቲያን አማንፑር ፈታኝ፣ ሞጋች በሆነ፣ በምርምር በተደገፈ የቃለ መጠይቅ ጥበብ የተካነች ናት፡፡በ40 ዓመታት የጋዜጠኝነት ሥራዋ፣ ክርስቲያን አማንፑር በርካታ ግጭቶችና ጦርነቶችን በሥፍራው በመገኘት ዘግባለች፤ ብዙ ተደማጭነት ያላቸው፣ ታዋቂ ሰዎችን ቃለ መጠይቅ አድርጋለች። በYou Tube ዕለታዊ ፕሮግራሟን Amanpour and Company የምታዘጋጅ ሲሆን በተለያዩ ማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ አራት ሚሊዮን ተከታዮች አሏት።ለሦስት ሳምንታት ስለዘለቀው በኢራን ውስጥ እየተካሄደ ስላለው ጦርነትና፥ አገሪቷ የትውልድ አገሯ እንደመሆኗ መጠን ጦርነቱን መዘገብ የፈጠረባትን የተደበላቀ ስሜትና ከሙያዋ ስነምጋባር አንፃር ያለውን አንደምታ ታስረዳለች። አሜሪካና እስራኤል ከኢራን ጋር እያካሄዱት ባለው ጦርነት ከተቀሰቀሰው ተቃውሞና ከዘገባዋና ቃለመጠየቅ ካደረገችላቸው ሰዎች በመነሳት፥ ተከፋፍለውና ተጻረው ቆመው የሚታዩት የኢራን ዲያስፖራ ማህበረሰብ ተገቢ ያልሆኑ ስድቦች እና የጥላቻ ንግግሮች እየደረሱባት ይገኛሉ። ከዚህ ቀጥሎ የቀረበው ከፈረንሳይ ጋዜጣ ሊቤራስዮን ጋር ያደረገችው ቃለመጠየቅ ነዉ።

እስራኤልና ዩናይትድ ስቴትስ በጋራ በኢራን ላይ የከፈቱት ጦርነት ከተጀመረ ሦስት ሳምንታት አልፎታል።ስለዚህ ግጭት ብዙ ግለሰቦችን ቃለ መጠይቅ አድርገሻል። እና ከተለያዩ አካላት የሰማሻቸው ትንታኔዎች እየሆነ ያለውን ነገር ለመረዳት አግዞሽ ይሆን?

ጦርነቱ ከተጀመረ ከሦስት ሳምንታት በኋላ፤ በርካታ ሰዎችን ባነጋግርም ጦርነቱ የተጀመረበትን መነሻ ምክንያት እስካሁንም ድረስ መረዳት አዳጋች ነው። የኢራን እስላማዊ ሪፐብሊክ ከፍተኛ መሪ አያቶላ አሊ ኻሚኒና ሌሎች ከፍተኛ ባለስልጣናት የካቲት 21 ላይ መገደል ለአሜሪካ እና እስራኤል የስለላ ሥራ ስልት ታላቅ ስኬት ነዉ።ከአጠቃላይ ግቡ አንፃር ግን የተሣካለት የሚባል አይደለም።የአገዛዙ መዋቅር አሁንም እንዳለ ነው።መጀመሪያ ላይ የነበረው እቅድ የአገዛዙ አናት ሲቀነጠስ ሌላዉ አካል ይፈረካከሳል የሚል ነበር። ያ እስካሁን አልሆነም።በርግጥ አገዛዙ በከፍተኛ መጠን ተዳክሞአል። ግን የኢራን አገዛዝ ለረጅም ዓመታት ዘላቂ እና በቀላሉ የማይወድቅ የኃይል መዋቅር ለመፍጠር ችሏል።እስራኤልንና የአሜሪካ የጦር ሰፈሮች፣ ለመምታት ሚሳኤሎች፣ ኢኮኖሚያዊ ኢላማዎች ላይ ያነጣጠሩና ጥቃቶችን ለመፈፀም ዝግጅቶችን ሲያደርግ ቆይቷል። ትራምፕ ኢራን በፍጥነት እጅ አለመስጠቷ መገረምን ፈጥሮበታል።አቅልሎም አይቷቸው ነበር።

በቦታው ላይ ያሉት ሰዎች ምን ይላሉ?
በቴህራን ውስጥ በፍርሃት ተውጠው እንቅልፍ መተኛት የማይችሉ ብዙ ሰዎችን ማነጋገር ችያለሁ።የኢራን ባለስልጣኖች፥ መንግስትን በመቃወም ማንኛውም አይነት ሰላማዊ ሰልፍ፥ እንዳይደረግ በመከልከል ተጠምደዋል። ለማደርግ የሞከሩ እንደ ከዳተኞች ይቆጠራሉ።አንድ የፀጥታ ሃይል አባል፥ እንደተናገረው ለተቃውሞ የሚወጡ ሰዎች ላይ በቀጥታ እርምጃ እንዲወሰድ ትዕዛዝ ተሰጥቷል። በጥር ወር አገር አቀፍ ተቃውሞ በባለሥልጣናት ከፍተኛ የኃይል እርምጃ ተወስዷል። አሜሪካ እና እስራኤል በከፈቱት ያልተቋረጠ ጥቃት ደግሞ በርካታ ስቪሎች ተገድለዋል። ታሪካዊ ቅርሶች ላይ ከፍተኛ ጉዳት መድረሱ ብዙ ቁጣ አስነስቷል፡፡እንደዚህም ሆኖ፥ የአሜሪካ ብሔራዊ ስለላ መሥሪያ ቤት፤ የኢራን መንግሥት መዋቅር እንዳለ መሆኑን ተናገግሯል።

አንቺ መነሻሽ ከኢራን ነው።የኢራን መንግስት በራሱ ህዝብ ተቃውሞ እየገጠመው ነበር፣ ጥር ወር እጅግ ደም አፋሳሽ ነበር። አሁን ጦርነቱ ከተጀመረ በኋላ ያለውን ሁኔታ እንዴት ትመለከችዋለሽ?

ለእኔ ከባድ ነው።ያደግኩት በኢራን ነው። ከአብዮቱ ጥቂት ቀደም ብሎ ኢራንን ለቅቄ ወጣሁ።አያቶላህ ካሆሜኒ በጥር 1979 ከመመለሳቸው ጥቂት ሳምንታት ቀደም ብሎ።ወላጆቼ እና እህቴ እስከ ሳዳም ሁሴን ወረራ ድረስ እዚያው ቆዩ። ከዚያም ሁሉም አገሪቱን ለቀው ወጡ። ከዚያ በሗላ ባሉት ዓመታት፥ ለሲኤንኤን ለመዘገብ ወደ አገሪቱ ብዙ ጊዜ ተመላልሻለሁ።ያለ ፍርሃትና ያለማዳላት የጋዜጠኝነትን ሥራ መሥራት መቻል ትልቅ ዋጋ አለው።እኔ የፖለቲካ አክቲቪስት አይደለሁም።አገሬ ናት፤ ንፅሗን ላይ የሚደርሰው ነገር በጣም ያሳስበኛል።ባህላዊና ታሪካዊ ቅርስ ላይ ጥቃት ሲደርስ ልቤን ይሰብረዋል።ነገር ግን ለዚህ ወይም ለዚያኛው አይነት የፖለቲካ አቅጣጫ ቅስቀሳ ማድረግ የእኔ ስራ አይደለም።የእኔ ስራ እየሆነ ያለውን ማንኛውንም ነገር ከተለያየ አቅጣጫ በመመልከት ሸፋን መስጠት ነው።በእርግጥ የኢራንን ህዝብ ሰብአዊነት አጉልቼ ማቅረብ እፈልጋለሁ።እስላማዊው ሪፐብሊክ ሥልጣን ላይ ከተቆናጠጠ ካላፉት 47 ዓመታት ጀምሮ 90 ሚልዪን የሚደርሰው የኢራን ሕዝብ፥ ጨቋኝ እስላማዊ አስተዳደር እንዲሰፍን ፍላጉት እንዳለው አድርጐ ማቅረብ የተለመደ ነው።አብዛኞቹ ኢራናውያን የሚፈልጉት ዲሞክራሲ፣ ኑሮአቸውን ማሻሻልና ልጆቻቸውን በነፃነት ማሳደግ ነው።ትራምፕ አገዛዙን ብቻ ሳይሆን ህዝቡንም በመጨመር አፀያፊ ስድብ እየተሳደበ ነው። ኢራናውያን ዲያብሎሶች ሲል ጠርቷቸዋል፤ የአሜሪካው መከላከያ ሚኒስትር ፒት ሄግሴት ኢራናውያን አረመኔ ሲል ተሳድቧል።

ከኢራኑ ሻህ ልጅ፤ ሬዛ ፓህላቪ ጋር ባደረግሽው ቃለመጠየቅ በደጋፊዎቹ ዘንድ ብዙ ትችቶችን አስተናግደሻል።ስለዚህ ጉዳይ ምን ትያለሽ?
ለእንዲህ አይነት፥ መሠረተ ቢስ ውንጀላዎች ብዙ ክብደት አልሰጣቸውም። እኔ ያንዱ ወይም የሌላው የፓለቲካ ፓርቲ ደጋፊ አይደለሁም።በሙያዬ ሁሉ ትክክለኛ እና ሚዛናዊ ዘገባዎችን ለማቅረብ ስሰራ ነበር።ኢራን በሄድኩበት ጊዜ እንኳ የራሴን ነፃነት አደጋ ላይ በመጣል ሥራየን አከናውን ነበር።በ2000 ሙሃመድ ካታሚ ሦልጣን ላይ በነበሩበት ጊዜ የኢራን ወጣቶችን ምኞቶች የሚያንፀባርቁ ዘገባዎችን እሰራ ነበር።በዩኒቨርሲቲ ውስጥ ይደረጉ የነበሩ ውይይቶች፣ ወጣቶች ለአልኮል መጠጥ ምን አመለካከት ሊኖራቸው ይገባል? ዓይነት።በዚህ ምክንያት ለአምስት ዓመታት ያህል ወደ ሀገሪቱ እንዳልገባ ታግጃለሁ።እና ከዚያ በ2009 አረንጓዴ ንቅናቄ በመባል የሚታወቀው የምርጫ ተቃውሞ ጊዜ ተመለስኩ። በዚህ ጊዜ፥ በገዥው አካል የተለያየ ማስፈራርያ እና ዛቻ ደርሶብኛል። አገሩን ጥየ ካልወጣሁ እንደሚያስሩኝ ነገሩኝ።እስከ ዛሬ ድረስ፥ ወደ አገሪቱ እንድገባ አይፈቀደልኝም።በመስከረም 2022 ፕሬዘዳንት ኢብራሂም ራይሲ የተባበሩት መንግሥታት ጠቅላላ ጉባኤን ለመታደም ወደ ኒው ዮርክ ሲያመሩ፥ በብቸኝነት ቃለ መጠይቅ ለማድረግ ዕድል አግኝቼ ነበር። ከቀናት በፊት ማህሳ አሚኒ የተሰኘች ሴት ፀጉርሽን አልሸፈንሽም በሚል በሃይማኖታዊ ፖሊሶች ቁጥጥር ሥር ከዋለች በኋላ ሕይወቷ ማለፉን ተከትሎ በተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች አመጽ ተቀጣጥሎ ነበር። ቃለ መጠይቁ ከመደረጉ ጥቂት ሰዓታት በፊት፣ ፀጉሬን እንድሸፍን በመጠየቄ ቃለ መጠይቁን ሰርዤዋለሁ። ፀጉሬን ሳልሸፍን ፕሬዝዳንቱ ሊቀመጡበት ተዘጋጅቶ የነበረ ባዶ ወንበር ፊት ለፊት ተቀምጬ የሚያሳይ ፎቶ ለጥፌያሁ።

የሬዛ ፓህላቪ ደጋፊዎች በቃለመጠየቁ፥ ለምን እንደተበሳጩ አልገባኝም።ሀሳቡን እንዲገልፅ ዕድል ሰጠሁት፤ እሱ ራሱ ደስተኛ እንደሆነ ነግሮኝ ነበር።በቃለ መጠይቁ ምክንያት፥ በኢራን መንግስት ተችቻለሁ።የንጉሣዊው አገዛዝ ደጋፊዎች ጥላቻን ያዘሉ ንግግሮች መንዛታቸው ለራሳቸውም ጥሩ አይደለም። አላማቸውን ለማሳካት ከማገዝ ይልቅ የሚጏዳቸው ሆኖ ይሰማኛል።

በተለያየ ጽንፍ የተከፋፈለው የኢራን ዲያስፖራ በዘላቂ የአገሪቱ ጥቅሞች ላይ አንድ ላይ መቆሙ ቀርቶ፤ ተጻራሪና ግዚያዊ የሆኑ የቡድን ፍላጎቶችን ይዞ በየፊናው መቆሙ፥ ለሀገሪቱ አማራጭ ኃይል ለማግኘት ይከብዳት ይሆን ?

እርግጥ ነው፣ እንዲህ ዓይነቱ ክፍፍል የሽግግር መንግስት ለመመስረት አያግዝም።የሕዝብ አመኔታ ያለው፥ ተቃዋሚ ስንሆን የመጀመሪያው ህግ፥ ሰዎችን ከመከፋፈል ይልቅ ወደ አንድነት ማምጣት ነው።ኢራን የተለያየ ብሄረሰቦች ያሏት ሀገር ነች፤ እንደ ተቃዋሚ ፓርቲ ከሁሉም ጋር ለመስራት ዝግጁ መሆንዎን ማሳየት ይኖብርሃል።

ጦርነቱ በአዎንታዊ መልኩ ሊያበቃ ይችላል?
ለመናገር ይከብዳል።በዲያስፖራ ያሉ የኢራን ንጉሣዊ ቤተሰብ አስተዳደሩ በሕዝብ እንቅስቃሴ ይፈርሳል ብለው ተስፋ ያደርጋሉ። እስራኤል በመቶዎች የሚቆጠሩ ሰው አልባ አውሮፕላኖች እና ሚሳኤሎችን በመተኮስ ባሲዲጂ የተባለውን የኢራን እስላማዊ አብዮታዊ ጓድ በመደብደብ ኢራናውያን አስተዳደሩን እንዲያፈርሱ ለማመቻቸት ሞክረው ነበር።
ሌላው ዓላማ፣ ኢራን ያከማቻቸውን 440 ኪሎ ግራም የበለፀገ ዩራኒየም ማግኘት ነው። አንድ የትራምፕ የቀድሞ አማካሪ እንደነገረኝ አሜሪካ የክምችቱን ቦታ ለማግኘት ትፈልጋለች።የእስራኤል ዓላማም ይሄ ነውን? እስራኤል በሊባኖስ አዲስ ግንባር ከፈታለች። ሁኔታው አስቸጋሪ ሁኔታ ነው።

Share this post