ቶታል በጦርነቱ ከፍተኛ ትርፍ ለመሰብሰብ ቻለ

ቶታል በጦርነቱ ከፍተኛ ትርፍ ለመሰብሰብ ቻለ

ምንም እንኳን አሜሪካ እና እስራኤል በኢራን ላይ የከፈቱት ጦርነትና የኢራን አፀፋ በብዙ ሀገራት ላይ ኢኮኖሚያዊ ቀውስም ቢያስከትልም ፣ እንደ ቶታል ላሉ ኩባንያዎች ግን ትርፍን እያስገኘላቸው ነው።
የሆርሙዝ የባሕር ወሽመጥ ሊዘጋ እንደሚችል ቀድሞ በመገመት፥ የነዳጅ አከፋፋይ ኩባንያ የሆነው ቶታል ኢነርጂ በመካከለኛው ምስራቅ የነዳጅ ክምችትን በመግዛት ከ1 ሚልያርድ ዶላር በላይ ትርፍ ለመሰብሰብ እንደቻለ ‘ፋይናንሻል ታይምስ’ የተባለው ጋዜጣ ዘግቧል።

የፈረንሳዩ ግዙፉ የነዳጅ ድርጅት፣ ቶታል በተባበሩት አረብ ኤምሬቶች እና በኦማን የሚመረቱ 70 የሚጠጉ ድፍድፍ ነዳጅ ካርጐዎችን የካቲት ወር ላይ ገዝቷል። በጥር ወር ከገዛው በእጥፍ በበለጠ።

እስራኤልና ዩናይትድ ስቴትስ በ8 ወራት ዉስጥ ለሁለተኛ ጊዜ በኢራን ላይ የከፈቱት ጦርነት ወሳኝ የነዳጅ መተላለፊያ የሆነው የሆርሙዝ ወሽመጥ በመዘጋቱ ከፍተኛ የዋጋ ጭማሪ እና የአቅርቦት ቀዉስ አስከትሏል። ከ130 አገራት በላይ ማደያዎች ያሉት ግዙፉ የቶታል ኢነርጂስ ከዚህ ቀደም ታይቶ በማይታወቅ መልኩ ትልቁ ግዢዎችን መፈፀም የጀመረው በዚህ አጋጣሚ ነው።

እንደ ፋይናንሻል ታይምስ ዘገባ፤ የዱባይ ድፍድፍ ዘይት በርሜል ዋጋን የሚወስነው S&P Global Platts የተባለው ድርጅት ከማርች ሁለት ጀምሮ በሆርሙዝ የባሕር ወሽመጥ የሚያልፈውን የየፔትሮል ዎጋ ትመና ስራውን ያቆመ ሲሆን ቶታል በተባበሩት አረብ ኤምሬቶች እና በኦማን የሚመረቱ 70 የሚጠጉ ድፍድፍ ነዳጅ ካርጐዎችን የካቲት ወር ላይ ገዛ።ያም ድርጅቱን 870 ሚልዩን ዩሮ በሁለት ሳምንታት ብቻ እንዲያገኝ አድርጐታል።

እንደ ቶታል ሁሉ፥ በጦርነቱ ለማትረፍ እየምከሩ ካሉት Powerus የተባለው ድርጅት ንብረትነቱ በፕሬዚዳንት ትራምፕ ልጆች የተያዘ ነው። ድርጅቱ ለአሜሪካ መከላከያ መስሪያ ቤት ፔንታጐን የድሮን አውሮፕላኖች አቅራቢ ሆኖ እንዲመረጥ በመፎካከር ላይ ይገኛል። ይህ ድርጅት ከተሳካለት፥ ፔንታጎን ለሰው አልባ አውሮፕላኖች የማምረቻ ማዕከል ለመገንባት ከመደበው 1.1 ቢሊዮን ዶላር የተወሰነውን መጋራት ይችላል።

Share this post

Post Comment