ዮክሬን በሩሲያ መዲና ላይ ግዙፉ የድሮን ጥቃት ፈጸመች

ዮክሬን በሩሲያ መዲና ላይ ግዙፉ የድሮን ጥቃት ፈጸመች

ዩክሬን ለሁለት ተከታታይ ምሽቶች ምስኮ ላይ የድሮን ጥቃት ፈፀመች

የሩሲያ መከላከያ ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ ባለፉት 24 ሰዓታት ወደ 926 የሚጠጉ የዩክሬን ድሮኖችን ማክሸፉን አስታውቋል፤ ይህም ጦርነቱ ከተጀመረ ጀምሮ ዩክሬን ካደረሰቻቸው ጥቃቶች ሁሉ ግዙፉ እንደሆነ ተነግሮለታል።

የሞስኮ ከንቲባ ሰርጌ ሶብያን እንዳሉት፣ ከእሁድ ምሽት ጀምሮ 350 የዩክሬን ድሮኖች ወደ ከተማዋ ተተኩሰዎል፤ አብዛኞቹ ግን በአየር መከላከያ ተመትተው ወድመዋል። የሞስኮ ክልል አስተዳዳሪ አንድሬይ ቮሮብዮቭ እንዳሉት፣ በጥቃቱ ሦስት ሰዎች ሲሞቱ ሌሎች አምስት ቆስለዋል።

ዩክሬን በሩሲያ የኃይል መሠረተ ልማቶች ላይ የምትፈፅመው ረጅም ርቀት ተጓዥ የድሮን ጥቃቶች ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ እየጨመሩ ሲሆን፤ የሩሲያን የጦር አቅም ለማዳከምና ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲንን ወደ ሰላም ድርድር እንዲገቡ ግፊት ለማሳደር ነው።

ኪዬቭ በጥቃቷ ሰፊ የነዳጅ እጥረት እንዲከሰት አድርጋለች።ከሶቪየት ህብረት መፈራረስ ወዲህ ሩሲያ ያጋጠማት እጅግ የከፋ የተባለለት የነዳጅ ቀውስ። በዚህም ምክንያት ባለሥልጣናት በመላ አገሪቱ የነዳጅ ሽያጭ በምጠና እንዲከፋፈል ሲወስኑ፣ እንዲሁም ነዳጅ ወደ ውጭ መላክን ከልክለዋል።

ሩሲያ አብዛኞቹን ድሮኖች ሞስኮ ከመድረሳቸው በፊት መትታ መጣሏን ብትገልጽም፣ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በተከታታይ የድሮን ጥቃት ዒላማ መሆኗ የአየር ጥቃት መከላከያ መሣርያዎቿ ብቃት ላይ ጥያቄዎችን አስነስቷል።

የሞስኮ አራቱም ዋነኛ አውሮፕላን ማረፊያዎች የድሮን ጥቃቱን ተከትሎ ለሰዓታት መዘጋታቸው ተገልጿል።

የዩክሬን ጠቅላላ ጦር ሃላፊ እንደገለጹት፣ ቅዳሜና እሑድ በተካሄዱ የድሮን ጥቃቶች በሩሲያ ውስጥ የሚገኙ በርካታ ወሳኝ ወታደራዊና የሎጂስቲክስ ተቋማት ዒላማ ተደርገው ተመትተዋል። ከእነዚህም መካከል በሩሲያ የሳማራ ክልል የሚገኘው የሲዝራን የነዳጅ ማጣሪያ ማዕከል ይገኝበታል ብለዋል።

የዩክሬን ድሮኖች በአዞቭ ባሕር ውስጥ 10 የሩሲያ የነዳጅ ጫኝ መርከቦችን እና 4 መርከቦችን መምታታቸውን የዩክሬን ጠቅላላ ጦር ሃላፊ ገልፀዋል።

ሰኔ 25 ቀን ፕሬዚዳንት ቮሎዲሚር ዘሌንስኪ 40 ቀናት የሚቆይ የ«ተጽዕኖ ማሳረፊያ ዘመቻ» (influence operation) መጀመሩን ያስታወቁ ሲሆን በሩሲያ ቁጥጥር ስር ባሉ አካባቢዎች ያሉ ስትራቴጂካዊ ማዕከላት ላይ መካከለኛ የመወንጨፍ አቅም ያላቸው ሚሳኤሎች ማስወንጨፍን መጠቀምን ያካትታል። ዓላማው ክሪሚያን መክበብ እና በግንባር ላይ ለሚገኙ የሩሲያ ወታደሮች የሚደርሱ የትጥቅና ስንቅ አቅርቦትን ማስተጓገል ነው።

የዩክሬን የሰው አልባ መሣርያዎች ዘርፍ ሃላፊ፥ ሮበርት ብሮቭዲ ሰኞ ጠዋት በማኅበራዊ ሚዲያ ባወጡት ጽሑፍ፣ በአዞቭ ባሕር 15 የሩሲያ የሕገ-ወጥ መርከቦች በድሮኖች ሌሊቱን መመታታቸውን ገልፀዋል። በተጨማሪም፣ በስምንት ቀናት ውስጥ በአጠቃላይ 105 መርከቦች ዒላማ መደረጋቸውን አስታውቀዋል። “የሩሲያ መርከቦች በየሌሊቱ ጥቃት እየደረሰባቸው ነው፤ በኬርች ባሕር ዳርቻ በኩል የሚደረገው እንቅስቃሴ ተቇርጧል፣ እንዲሁም የማራገፍ ሥራዎች እጅጉን ወርደዋል” ብለዋል።

ሩሲያም እሁድ ሌሊት እና ሰኞ ማለዳ ዩክሬንን በቦምብ ደብድባለች። ሆኖም ይህ ጥቃት ከቅርብ ጊዜያት የሩሲያ ጥቃቶች አንፃር፥ የተጠቀሙት የሚሳይልና የድሮን ብዛት አነስ ያለ ነበር። የዩክሬን አየር ኃይል እንደገለጸው፣ ሩሲያ ከክሪሚያ አየር ክልል ሦስት የአውሮፕላን ሚሳይሎችን እንዲሁም 134 የሻሄድ ድሮኖችን አስወንጭፋለች። የአየር መከላከያ መሣሪያዎች ሩሲያ በተለያዩ ግዛቶች ካስወነጨፈቻቸው 3 ሚሳኤሎች እንዲሁም ደግሞ 123 ሰው አልባ አውሮፕላኖች መትቶ መጣሉን የዩክሬን አየር ኃይል አስታውቋል።

የጥቁር ባሕር ወደብ ፈርጥ፣ ስትራቴጂያዊ ጠቀሜታ ያላት ኦዴሳ ከዒላማዎቹ መካከል አንዷ ነበረች።የክልሉ አስተዳዳሪ ኦሌህ ኪፐር እንደገለጹት፣ መንገዶች፣ የባቡር መስመሮች፣ ጉዳት ደርሶባቸዋል።በእሳት የተቃጠሉ በርካታየ አውቶቡሶችን ፎቶዎች አጋርተዋል። ቢያንስ ሦስት ሰዎች ቆስለው ወደ ሆስፒታል ገብተዋል።

Share this post

Post Comment