ትራምፕ፣ታዋቂዋ የቴሌቪዥን ጋዜጠኛ ከስራ እንድትባረር ግፊት እያደረጉ ነው

ትራምፕ፣ታዋቂዋ የቴሌቪዥን ጋዜጠኛ ከስራ እንድትባረር ግፊት እያደረጉ ነው

የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ፣ ታዋቂዋ የኤንቢሲ ቴሌቪዥን ጣቢያ ጋዜጠኛ ክርስቲን ዌልከር ከስራ እንድትባረር ግፊት እያደረጉ ነው።በምታቀርበው ዘገባ በመበሳጨት፣ በተደጋጋሚ የስድብ መዓት የሚያወርዱባት ትራምፕ አሁን ግን ጋዜጠኛዋ ለአሜሪካ የሚዲያ ይዘቶችን ተቆጣጣሪ ባለሥልጣን (The Federal Communications Commission) ስሞታ በማቅረብ ከስራ እንድትባረር ግፊት ጀምረዋል።

“የማትወደደው፥ በአንድ ወቅት ተወዳጅ የነበረው የ Meet the Press ፥ አሁን ግን Meet the Fake Press የሆነው ፕሮግራም አዘጋጅ ፥ ክርስቲን ዌልከር ፤ ትራምፕ ድጋፋቸውን የገለፁላቸው የምርጫ ተወዳዳሪዎች ያገኙት ውጤት አንድ ወጥ ያልሆነ ውጤት ነው ያመጣው ብላለችል።የዳርሊን ግራሃም እና ማይክ ማዜይ የቅርብ ጊዜ ድል ለሴኔቱ 100 ፐርሰንት፣ ለዩናይትድ ስቴትስ ምክር ቤት 98 ፐርሰንት ነው” ሲሉ ትራምፕ በትሩዝ ሶሻል (Truth Social) ገጻቸው ላይ ጽፈዋል።

ትራምፕ አክለውም፦ «በዚህ ሆን ተብሎ በተላለፈ የተሳሳተ መረጃ ምክንያት፣ የማስጠንቀቂያ እና ቅጣት እርምጃ እንዲወሰድባት ለFCC ሪፖርት ይደረጋል። እንደ አለመታደል ሆኖ ይህን የምታደርገው፣ እሷ ብቻ አይደለችም።»

ኤንቢሲ «ክሪስተን ከምርጥ ባለሙያዎቻችን አንዷ ናት፤ እኛም እሷን እንደግፋታለን።»የሚል መግለጫ አውጥቷል።

ምንም እንኳን ትራምፕ በማህበራዊ ሚዲያ ላይ ይህን ቢሉም፣ FCC በዌልከር ላይ እንደ ግለሰብ እርምጃ ለመውሰድ ሕጋዊ ሥልጣን የለውም። ሆኖም የትራምፕ አስተያየት በጋዜጠኛዋ ላይ እያደረጉት ያለውን ዘመቻ መጠናከሩን ያሳያል።

በሰኔ መጀመሪያ ላይ ትራምፕ ከጋዜጠኛዋ ዌልከር ጋር ያደረጉትን “Meet the Press” ቃለ ምልልስ በድንገት በመሀል አቋርጠው በመውጣት አነጋጋሪ ሆነው ነበር።

Share this post

Post Comment