የአሜሪካ ባህል እና ታሪክ እንዴት መንፀባረቅ አለበት የሚለው ጥያቄ ፖለቲካዊ አንደምታ እየያዘ እና ከፉፉይ አጀንዳ እየሆነ ነው።ከተለያዪ አለማት የተሰባሰቡ ዜጎች ያለሟት እና ኃያል ያደረጏት አገር፤ ፍትሃዊ በሆነ መልኩ የሕዝቧቿን ተሳትፎ እንዴት መዘከር አለባት የሚለው ርዕስ በተለያየ መስክ የተሰለፋ የፖለቲካ ሃይሎችን እያናቆረ ነው።ቢከፉም ቢለማም፤ ልዪነታቸውን አቻችላ ማኖር የቻለችው አሜሪካ ለሁሉም ነዋሪዎቿ እኩል መብት ትሰጣለች ማለት አይደለም።ያላፈ ታሪካቸውንም እንደዚሁ ተመሳሳይ ትኩረት አትሰጠውም።የየትኛው ወገን ታሪክ መጉላት አለበት የሚለው ርዕስ ሁሉንም አያግባባም። የተወሰኑት ወገኖች በማህበረ-ኢኮኖሚያዊ እና ፖለቲካዊ ገጽታ የ “ተገለናል” መንፈስ ተላብሶአቸው ቆይቷል።የተለያዩ ያለፉት መንግሥታት ሁኔታውን ለማሻሻል ጥረት ሲያደርጉ ቆይተዋል። ትኩረት የተነፈገው እና ከዚህ ቀደም ትኩረት ባልተሰጣቸው ሕዝቦች ጉዳይ ላይ የተወሰነ መሻሻል ታይቷል።
በተወሰነ መልኩ መሻሻል ሲታይ፣ በሌላ መልኩ ወደ ኋላ መመለስ ይታያል። እንዲህ አይነት ፍትጊያዎች እና አታካራዎች ከሚካሄዱባቸው ሥፍራዎች አንዱ ከዋይት ሃውስ ብዙም ሳይርቅ የሚገኘው ስሚስዮናን (Smithsonian) ብሔራዊ ሙዚየም ነው። በመሃል ዋሽንግተን ዲ.ሲ. የሚገኘውን ረጅም የእግር መንገድ (National Mall) አልፎ የሚገኘው ስሚስዮናን፣ የዶናልድ ትራምፕ አዲስ የፕሬዚዳንት አስፈጻሚ ትዕዛዝ (አዋጅ) ዒላማ ሆኗል።
ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ሐምሌ 17, 2018 (July 24, 2026) ዓ.ም. “ ስሚስዮናን ተቋም ላይ የነበረው አመኔታ ቀድሞ ወደነበረበት መመለስ” “Restoring Trust in the Smithsonian Institution” በሚል ርዕስ የፕሬዚዳንታዊ ትዕዛዝ (Executive Order) አውጥተዋል። በፌዴራል መንግሥት የሚደገፉ ሙዚየሞች፥ የአሜሪካ ታሪክን አቀራረብ እንዲቀይሩ ለማድረግ እየተካሄዱ ካሉ ዘመቻዎች አንዱ አካል ነው።ትራምፕ አስተዳደራቸው “ትክክለኛ ያልሆኑ” ብሎ የሚፈርጃቸውን የሙዚየሙ ኤግዚቢሽኖች በተመለከተ ጎብኚዎችን ቀድሞ ለማስጠንቀቅ፣ በመግቢያው ላይ ምልክቶች እንዲቀመጡ አዝዘዋል።
የትራምፕ የአስፈጻሚ ትዕዛዝ የዋይት ሀውስ የሀገር ውስጥ ፖሊሲ ምክር ቤት ያዘጋጀውን ሪፖርት በማስረጃነት ጠቅሷል።ሪፖርቱም ሙዚየሙን “ፀረ-አሜሪካዊ አስተሳሰብ ማሳያ” እና “ተቋሙ ገለልተኛ ሚናውንና ዓላማውን በመተው ወደ ፖለቲካዊ አክቲቪዝም የተሳተፈ ተቋም እየሆነ ነው” በማለት ከሷል። የስሚስዮናን ሙዚየም የአሜሪካንን ታሪክ ከፍ አድርጐ ማሣየት ሲገባው በማኮሰስ እና በማጠልሸት ሥራ ተጠምዷል ሲል ከሷል።
ይህንን ለማስፈፀም በብሔራዊ ፓርክ አገልግሎት (National Park Service) ስር ባሉ የእግረኛ መንገዶች ላይ፣ “በሙዚየሙ የሚቀርቡ ስህተቶች” ለማስተካከል ምልክቶች እንዲተከሉ ለባለሥልጣናት መመሪያ እንደሰጠ ተናግሯል። የፓርክ አገልግሎቱ በውስጥ ጉዳይ ሚኒስትሩ የሚተዳደር ሲሆን፣ 180 ዓመት ያስቆጠረው ስሚስዮናን ግን ነፃ እና ገለልተኛ ተቋም ነው።ታዛቢዎች ይህ የአሜሪካንን ታሪክ ከወግ አጥባቂ አመለካከት አንፃር ለማቅረብ እየተካሄደ ያለ ሰፊ ዘመቻ አካል ነው ይላሉ።ትራምፕ በትዕዛዛቸው፣ የስሚስዮናን ተቋምንና የሙዚየሙን አመራሮች የአሜሪካንን ታሪክ በታማኝነትና ተገቢ ዕውቅና በመስጠት ለማቅረብ እምነት ሊጣልባቸው እንደማይችል ገልፀዋል።
የሙዚየሙ ዳይሬክተር አንቲያ ሃርቲግ፣ የዋይት ሀውስ ሪፖርት የሙዚየሙን ሥራ በአግባቡ እንዳልገለጸው እና በኢ-ፍትሃዊ መንገድ እንዳቀረበው ተናግረዋል።ሃርቲግ በዩናይትድ ስቴትስ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ንዑስ ኮሚቴ ፊት ቀርበው ራሳቸውን ተከላክለዋል።ሙዚየሙ የሀገር ፍቅርን ‘በትዕዛዝ ሳይሆን በተነሳሽነት’ ሲያስተላልፍ ነው ተፅዕኖ ሊያሳድር የሚችለው ብለዋል።
በርካታ የታሪክ ተመራማሪዎችን በአባልነት ያካተተው የአሜሪካ ታሪክ ማኅበር (American Historical Association)፣የስሚስዮናን ተቋም በሳይንሳዊ ጥናት በመታገዝ ትክክለኛ መረጃዎችን ለማቅረብ የሚያደርገውን ጥረት አድንቋል።