የትራምፕ አለም ዋንጫ

የትራምፕ አለም ዋንጫ

በአሜሪካ፣ ሜክሲኮ እና ካናዳ በጣምራ አስተናጋጅነት በሚካሄደው የ2026 ዓለም ዋንጫ ሊጀመር ሰዓታት ቀን ብቻ የቀረው ሲሆን እንደ አሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ የጫዎታውን መጀመር በጒጒት የሚጠባበቅ ሌላ ሰው የለም።የፊፋው ፕሬዝዳንት ጂያኒ ኢንፋንቲኖ አዲሱን የፊፋ የሰላም ሽልማት ለትራምፕ ማበርከታቸው፤ የዚህን የአለም ዋንጫ ችግር ማሣያ( metaphor) ነው በማለት የሂውማን ራይት ዎች ሚንኪ ዎርደን ተናግረዎል።ትራምፕ ሽልማቱን በተቀበሉ በጥቂት ቀናት ውስጥ በቬንዙዎላ እና በኢራን ላይ ጦርነት ማወጃቸው ይታወሳል።ትራምፕ እንደ ማራዶና፣ ፔሌ እና ሜሲ የአለም ዎንጫው ኮከብ ሆነው መውጣት ይፈልጋሉ፡፡አገራቸው ዎነኛዋ አዘጋጅ በመሆን 78 ምርጥ ጫወታዎችን የምታሰናዳ ሲሆን ካናዳ እና ሜክሲኮ እያንዳንዳቸው 13 ጫወታዎችን ብቻ ነው የሚደርሳቸው።

በዚህ አለም ዎንጫ ተመልካቾችን ካበሳጫቸው ነገር አንዱ፤ የተቀመጠው የመግቢያ ዋጋ እጅጉን መወደዱ ነው፡፡ተራ ጨዋታዎችን እኮ ለማየት ክፍያው አላግባብ የተጋነነ በመሆኑ ጫወታዎቹን ስቴድም ገብተው ለመታደም ያሰቡ ደጋፊዎችን አበሳጭቷል።በዚህ ምክንያት ብዙ ያልተሸጠ ትኬት በመኖሩ እና ሆቴሎች ባዶ በመሆናቸው ለአዘጋጅ ሀገራቱ አሳሳቢ እንደሆነባቸው እየተዘገበ ነው።ሌላው ስጋት የአሜሪካ ኢምግሬሽን መኮንኖች ይህንን አጋጣሚ በመጠቀም የስደተኞች ማደኛ ያደርጉታል የሚል ነው።የኢሚግሬሽን እና ጉምሩክ ተቆጣጣሪ (አይስ) ተጠባባቂ ኃላፊ ቶድ ላዮንስ የኢምግሬሽን ፓሊሶች በጫወታዎቹ ሁሉ ፀጥታን በማስከበር ስራ ይሳተፉሉ ብለዋል።የሰብአዊ መብት ተሟጋቾች አይስ ይህን አጋጣሚ በመጠቀም የሜክሲኮ እና የኮሎምብያን ማሊያን የለበሱ ስደተኞች ሊያፍስ ይችላል የሚል ስጋት አድሮባቸዋል።

በዓለም ዋንጫ የመጀመሪያው ሶማሊያዊ ዳኛ ይሆናል ተብሎ ሲጠበቅ የነበረው ኦማር አርታን አሜሪካ እንዳይገባ መታገዱ፣ የሴኔጋል ከዎክብት ከአውሮፕላን ማረፊያ ሲወርዱ ልክ እንደአሸባሪ መበርበር ይህ የአለም ዎንጫ ምን ሊመስል እንደሚመስል ፍንትው አድርጎ የሚያሳይ ነው።ፊፋ በእነዚህ ሁሉ ጉዳዮች ላይ ምንም ተቃውሞ አላሰማም። ለዚህም ነው፤ የፈረንሳይ ጋዜጣ L’Equipe የፊፋን ፕሬዚዳንት ጂያኒ ኢንፋንቲኖ “የትራምፕ አሻንጉሊት” ተብሎ የተሳለቀበት።

Share this post

Post Comment