በቴህራን እና ዋሺንግተን መካከል ሲካሔድ የቆየው የሰላም ውይይት በስኬት መጠናቀቁ ይፋ በተደረገበት ወቅት፣ ሁለቱን ሀገራት ስታደራድር የነበረቸው ፓኪስታን ደስታዎን የገለፀችው በተቆጠቡ ቃላት ነበር።ጠቅላይ ሚኒስትሯ ሼህባዝ ሻሪፍ “ዛሬ ወደ ሰላም ለመድረስ የተደረገን እርምጃ አለም ለመመልከት ችሏል”ብለዋል።
ስምምነቱ ዘላቂ ወደሆነ እርቅ ያመራል ወይ፤ እንዲሁም በውስጡ የተካተቱት ነጥቦች እንዴት ይተገበራሉ የሚለው በሂደት የሚታይ ሲሆን ለጊዜው ግን ይህ የሰላም ስምምነት ቀጣይ እርምጃዎችን ለማፉጠን የሚረዳ እንደ አንድ መንደርደርያ ሆኖ ነው የታየው።ለመሆኑ ከዚህ ስምምነት አትራፊው ማነው? ተጎጂውስ?
ከ106 ቀናት ጦርነት በሓላ የተደረሰው ይህ የሰላም ስምምነት፥ትልቅ ድል ነው ይላሉ በርናር ኡርካድ የተባሉ ፈረንሳዊ የኢራን ጉዳዬችን ተከታታይ። “የሰላምም ሆነ የወዳጅነትም ጉዳይ አይደለም፤ በሩቅ ምስራቅ ሀገራት የአምሳ አመታት ታሪክ፤ የተፈጠረ የከፋ ቀውስን ለማርገብ በሁለቱ አገራት መካከል ተቻችሎ ለመኖር የተደረገ ውል ነው” ይላሉ ፈረንሳዊ ተንታኝ። ኢራን “ትልቋ ሠይጣን” እያለች ከምትጠራት አሜሪካ ጋር ለመፈራረም ያስቻለውን የጋራ ስምምነት፣ የሀገሪቱ ባለሥልጣናት በከፍተኛው የብሔራዊ ደኅንነት ምክር ቤት እንዲጸድቅ አድርገው ነበር። በዚህ የሰላም ስምምነት ከተከፉት ወገኖች መካከል የኢራን እስላማዊ አብዮታዊ ዘብ አክራሪ ክንፍ አንዱ ነው። እንደ ተንታኙ ገለጻ፣ የእነርሱ ፍላጎት ጦርነቱ እንዲቀጥል ነበር፤ ሆኖም ባይወዱትም ስምምነቱን ለመቀበል ተገደዋል።
“በውጭ ሀገራት የሚኖሩ የቀድሞው የዘውድ ሥርዓት ደጋፊዎችም በበውሉ አልተደሰቱም” ሲሉ ተንታኙ ያስረዳሉ።
በሌላ በኩል፣ የኢራን አስተዳደር የሰላም ውሉን ትልቅ ድል እንዳገኘ አድርጐ በማቅረብ ላይ ነው። የነዳጅ እና የተፈጥሮ ጋዝ መተላለፊያ የሆርሙዝ ወሽመጥ እንዲከፈት ለኢራን ጉልህ ኢኮኖሚያዊ ጥቅሞችን እንደሚያስገኝ ይጠበቃል። አሜሪካኖች፥ ውሉን ለመፈፀም፥ ትልቅ ፍላጐት አሳይተዋል። ሲጣደፉም ታይተዋል።ግን ያ ማለት ኢራኖች ድልን ተቀዳጅተዋል ማለት ነውን? እስራኤሎች የማይደግፉትን ስምምነት እንዲቀበሉ እየተገደዱ ነው ወይ?
“ይህ ስምምነት፥ ኢራናውያን የተጐናፀፉት ድል ነው ከማለት ይልቅ፥ አሜሪካኖች መሸነፋቸውን የሚያሳይ ነው” ይላሉ ጆናታን ፒሮን የተባሉት የኢራንን ጉዳይ የሚከታተሉ ተንታኝ። “አሜሪካና እስራኤል ተጣምረው፥ የኢራንን መንግስት ለመጣል አለመቻላቸው ብቻ፥ ሳይሆን፥ ይህ ጦርነት ኢራን ከነበረችበት፥ ምስቅልቅል ቀውስ፥ እንድትወጣ፥ ጥርጊያ መንገድ የሚከፍትላት ይመስላል” ይላሉ ተንታኙ።
“ጦርነቱ ከመቀስቀሱ በፊት፥ ሥርዐቱ እየተንገዳገደ ነበር፤ ከዚህ በፊት ታይቶ በማይታወቅ የህዝብ አመፅ እየታመሠ ነበር። አገዛዙ የሚደግፋቸው፥ በእስራኤል ዙሪያ በሚገኙ አገራት ውስጥ ያሉ ታጣቂ ቡድኖችን አከርካሪያቸው ተመትቶ በጣረሞት ላይ ነበሩ። የፍልስጤሙ ሐማስ፣ የሊባኖሱ ሔዝቦላህ፣ የየመኑ ሁቲ ቡድኖች ።
በተለይ፥ ይህ ጦርነት፥ እስላማዊቷ ሪፐብሊክ፥ አዳዲስ የማጥቂያ ዘዴዎችን፥ በተሳካ መልኩ እንድትጠቀም አግዟታል። ባሊስቲክ ሚሳይሎችን እና ድሮኖችን፥ በባህረ ሰላጤ ጎረቤቶቿ ላይ በመተኮስ፥ አገራቱ የመከላከያ ዘዴያቸውን መልሰው እንዲያጠኑ አድርጓቸዋል።
የተደረሰው ስምምነት ከኢራን ላይ ማዕቀቦችን ማንሳትን ያካትታል። ኢራን በሆርሙዝ ወሽመጥ የሚያልፉ መርከቦችን ማስከፈል ትጀምራለች። በቴሀራን ያለውን ኢንቨስትመንት ለማንቀሳቀስ በሚል ከፍተኛ መጠን ያለው ገንዘብ ይሰጣል። “የድርድሩ በጣም ቀላል ክፍል የተኩስ አቁም ስምምነት ነው።ነገር ግን የቀረው ክፍል አስተማማኝ አይደለም። “ይላሉ ጆናታን ፒሮን። የኢራን ጦርነት እንዲቀሰቀስ ዋነኛ ምክንያት የሆነው የኒውክሌር ፕርግራም 60 ቀናት ውስጥ ድርድር የሚካሄድበት ጉዳይ ይሆናል። በሌሎች ቁልፍ ጉዳዮች ላይም፥ ኢራን ተይዞባት የነበረ ገንዘቧን እንድታገኝ እና ማዕቀቦች እንዲነሱላት ድርድር ይደረጋል።