ሲአይኤ አያቶላህ አሊ ኻሜኒን ያሉበትን ቦታ እንዴት ሊለየው ቻለ?

ሲአይኤ አያቶላህ አሊ ኻሜኒን ያሉበትን ቦታ እንዴት ሊለየው ቻለ?

የኢራን እስላማዊ ሪፐብሊክ ከፍተኛ መሪ አያቶላ አሊ ኻሚኒ እና ሌሎች የኢራን ከፍተኛ ባለስልጣናት ግድያ በአሜሪካ እና በእስራኤል መካከል የተደረገ የቅርብ የስለላ መረጃዎችን ልውውጥ ውጤት ነው ። ዘ ኒው ዮርክ ታይምስ እንደዘገበው የአሜሪካው ማዕከላዊ የስለላ ድርጅት (ሲአይኤ) አሊ ኻሜኒን ለብዙ ወራት ያሃል ክትትል ሲያደርግባቸው ቆይቷል፣ ቀስ በቀስ ስለ መኖሪያቸው ቤታቸው እና የእለት ተእለት ውሏቸው ዝርዝር መረጃን እየሰበሰበ ነበር።

ለአሜሪካ መንግሥት ቅርብ የሆኑ ምንጮች ለጋዜጣው እንደተናገሩት፣ ሲአይኤ አያቶላህ አሊ ኻሜኒ ቅዳሜ በቴህራን የአመራር ቅጥር ግቢ በሚካሄደው የኢራን መንግሥት ከፍተኛ ባለስልጣናት ስብሰባ ላይ ለመሳተፍ ሃሳብ እንደነበራቸው አወቀ። አሜሪካ እና እስራኤል የታቀደውን ጥቃት ከስብሰባው ጋር እንዲገጣጠም በማሰብ፥ ቀደም ብሎ የተቆረጠውን ቀን በመተው፥ ከባህር ሰርጓጅ መርከቦች እና ቦምብ ጣይ አውሮፕላኖች የሚተኮሱትን መሳሪያዎች አቀናጅ። ቅዳሜ ለት ጠዋት ሁለት ሰዓት አካባቢ ከአየር እና ከባሕር ላይ በተወነጨፉ ሚሳዔሎች በዋና ከተማ ቴህራን ውስጥ የሚገኙ የተለያዩ ቦታዎች መቱ።ጥቃቱ በተፈፀመበት ወቅት ከፍተኛ የኢራን ብሄራዊ ደህንነት ባለስልጣናት በግቢው በአንድ ሕንፃ ውስጥ ነበሩ።ኻሚኒ በአቅራቢያው በሚገኝ ሌላ ሕንፃ ውስጥ። ባልጠበቀው ሁኔታ፣ ከሰማይ፣ ከውቅያኖስ እና ከየብስ የተሰነዘረ እጅግ የተቀናጀ የጥፋት ዶፍ በድንገት ከተማዋን አናወጣት። ላለፉት 37 ገደማ ዓመታት ሀገሪቱን የመሩት የ86 ዓመቱ አያቶላህ አሊ ኻሜኒ፣ የኢራን አብዮታዊ ዘብ አዛዥ ጀኔራል ሞሐመድ ፓክፖር እና የሀገሪቱ መከላከያ ምክር ቤት ጸሀፊ አሊ ሻምክኻኒ ተገደሉ።የኢራን ጦር ጠቅላይ አዛዥ ጄኔራል አብዶል ራሒም ሞሳቪ እና የመከላከያ ሚኒስትር ጄኔራል አዚዝ ናሲራዜህ በአየር ጥቃት ተገድለዋል።

“የኢራኑን ጠቅላይ መሪ በሚያስደንቅ ሁኔታ በፍጥነት ማስወገድ ጥቃቱ ከመድረሱ በፊት በዩናይትድ ስቴትስ እና በእስራኤል መካከል የነበረውን ጠንካራ ትበብር እና ቅንጅት የሚያሳይ ነው” ሲል ጋዜጣው ጽፏል። በተለይም ባለፈው ሰኔ ወር በተካሔደው የ12 ቀናት ጦርነትን ተከትሎ ነው የተጠናከረ ሲል ዘ ኒው ዮርክ ታይምስ ጽፏል። የኢራን መንግሥት ባለሥልጣናት እራሳቸውን ለመጠበቅ በቂ ጥንቃቄ እንዳልወሰዱ አሳይቷል” ጋዜጣው ጽፏል።

ስለ ኦፕሬሽኑ አካሄድ ማብራርያ የሰጡ ውስጥ አዋቂዎች፥ ይህ ጥቃት ጥሩ የመቀናጀት እና የወራት ዝግጅት ውጤት እንደሆነ ገልፀውታል። ባለፈው ሰኔ ወር የኢራንን የኒውክሊየር መርሃ ግብሯን ኢላማዎች ለመምታት እቅድ በማውጣት ላይ እንዳሉ፣ ፕሬዝዳንት ትራምፕ አሜሪካ አያቶላ ካሜኔይ የት እንደተደበቁ እንደምታውቅ እና ልትገላቸው እንደምትችል ተናግረው ነበር።ያ መረጃ የተገኘው ቅዳሜ እለት አሜሪካ ከተጠቀመችበት ተመሳሳይ ኔትወርክ ላይ ነው ሲሉ አንድ የቀድሞ የአሜሪካ ባለሥልጣን መናገራቸውን ጋዜጣው ዘግቧል።ከዚያን ጊዜ ጀምሮ ዩናይትድ ስቴትስ የምትሰበስበው መረጃ እየተሻሻለ መጥቷል ብለዋል።በተለይም ባለፈው ሰኔ ወር በተካሔደው የ12 ቀናት ጦርነትን ተከትሎ አሜሪካ፥ የከፍተኛ መሪው እና የኢራን እስላማዊ አብዮታዊ ዘብም በከፍተኛ ጫና ውስጥ እንዴት እንደገቡ እና ጦርነቱ የዕለት ተዕለት እንቅስቃሲያቸው ላይ ያሳደረውን ተጽዕኖ የበለጠ ማወቅ ቻለች ሲሉ የቀድሞው ባለስልጣን ተናግረዋል። ዩናይትድ ስቴትስ ያንን መረጃ በማካበት አያቶላ አሊ ኻሚኒን የመከታተል እና እንቅስቃሲያቸውን የመተንበይ ችሎታዋን አሳድጋለች።

Share this post

Post Comment