“ትራምፕ ኢራን በፍጥነት እጅ አለመስጠቷ መገረምን ፈጥሮበታል።”ክርስቲያን አማንፑር

“ትራምፕ ኢራን በፍጥነት እጅ አለመስጠቷ መገረምን ፈጥሮበታል።”ክርስቲያን አማንፑር

የኢራን ዝርያ ያላት አንጋፋዋ የሲኤንኤን ጋዜጠኛ ክርስቲያን አማንፑር ፈታኝ፣ ሞጋች በሆነ፣ በምርምር በተደገፈ የቃለ መጠይቅ ጥበብ የተካነች ናት፡፡በ40 ዓመታት የጋዜጠኝነት ሥራዋ፣ ክርስቲያን አማንፑር በርካታ ግጭቶችና ጦርነቶችን በሥፍራው በመገኘት ዘግባለች፤ ብዙ ተደማጭነት ያላቸው፣ ታዋቂ ሰዎችን ቃለ መጠይቅ አድርጋለች። በYou Tube ዕለታዊ ፕሮግራሟን Amanpour and Company የምታዘጋጅ ሲሆን በተለያዩ ማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ አራት ሚሊዮን ተከታዮች አሏት።ለሦስት ሳምንታት ስለዘለቀው በኢራን ውስጥ እየተካሄደ ስላለው ጦርነትና፥ አገሪቷ የትውልድ አገሯ እንደመሆኗ መጠን ጦርነቱን መዘገብ የፈጠረባትን የተደበላቀ ስሜትና ከሙያዋ ስነምጋባር አንፃር ያለውን አንደምታ ታስረዳለች። አሜሪካና እስራኤል ከኢራን ጋር እያካሄዱት ባለው ጦርነት ከተቀሰቀሰው ተቃውሞና ከዘገባዋና ቃለመጠየቅ ካደረገችላቸው ሰዎች በመነሳት፥ ተከፋፍለውና ተጻረው ቆመው የሚታዩት የኢራን ዲያስፖራ ማህበረሰብ ተገቢ ያልሆኑ ስድቦች እና የጥላቻ ንግግሮች እየደረሱባት ይገኛሉ። ከዚህ ቀጥሎ የቀረበው ከፈረንሳይ ጋዜጣ ሊቤራስዮን ጋር ያደረገችው ቃለመጠየቅ ነዉ።

እስራኤልና ዩናይትድ ስቴትስ በጋራ በኢራን ላይ የከፈቱት ጦርነት ከተጀመረ ሦስት ሳምንታት አልፎታል።ስለዚህ ግጭት ብዙ ግለሰቦችን ቃለ መጠይቅ አድርገሻል። እና ከተለያዩ አካላት የሰማሻቸው ትንታኔዎች እየሆነ ያለውን ነገር ለመረዳት አግዞሽ ይሆን?

ጦርነቱ ከተጀመረ ከሦስት ሳምንታት በኋላ፤ በርካታ ሰዎችን ባነጋግርም ጦርነቱ የተጀመረበትን መነሻ ምክንያት እስካሁንም ድረስ መረዳት አዳጋች ነው። የአሜሪካ ስሌት የተፈጠረውን አገዛዙን ለማስወገድ ከፈለጉ እርምጃ የመውሰድ ኃላፊነት ።

የኢራን እስላማዊ ሪፐብሊክ ከፍተኛ መሪ አያቶላ አሊ ኻሚኒና ሌሎች ከፍተኛ ባለስልጣናት የካቲት 21 ላይ መገደል ለአሜሪካ እና እስራኤል የስለላ ሥራ ስልት ታላቅ ስኬት ነዉ።ከአጠቃላይ ግቡ አንፃር ግን የተሣካለት የሚባል አይደለም።የአገዛዙ መዋቅር አሁንም እንዳለ ነው።መጀመሪያ ላይ የነበረው እቅድ የአገዛዙ አናት ሲቀነጠስ ሌላዉ አካል ይፈረካከሳል የሚል ነበር። ያ እስካሁን አልሆነም።በርግጥ አገዛዙ በከፍተኛ መጠን ተዳክሞአል። ግን የኢራን አገዛዝ ለረጅም ዓመታት ዘላቂ እና በቀላሉ የማይወድቅ የኃይል መዋቅር ለመፍጠር ችሏል።እስራኤልንና የአሜሪካ የጦር ሰፈሮች፣ ለመምታት ሚሳኤሎች፣ ኢኮኖሚያዊ ኢላማዎች ላይ ያነጣጠሩና ጥቃቶችን ለመፈፀም ዝግጅቶችን ሲያደርግ ቆይቷል። ትራምፕ ኢራን በፍጥነት እጅ አለመስጠቷ መገረምን ፈጥሮበታል።አቅልሎም አይቷቸው ነበር።

አንቺ መነሻሽ ከኢራን ነው።የኢራን መንግስት በራሱ ህዝብ ተቃውሞ እየገጠመው ነበር፣ ጥር ወር እጅግ ደም አፋሳሽ ነበር። አሁን ጦርነቱ ከተጀመረ በኋላ ያለውን ሁኔታ እንዴት ትመለከችዋለሽ?

ለእኔ ከባድ ነው።ያደግኩት በኢራን ነው። ከአብዮቱ ጥቂት ቀደም ብሎ ኢራንን ለቅቄ ወጣሁ።አያቶላህ ካሆሜኒ በጥር 1979 ከመመለሳቸው ጥቂት ሳምንታት ቀደም ብሎ።ወላጆቼ እና እህቴ እስከ ሳዳም ሁሴን ወረራ ድረስ እዚያው ቆዩ። ከዚያም ሁሉም አገሪቱን ለቀው ወጡ። ከዚያ በሗላ ባሉት ዓመታት፥ ለሲኤንኤን ለመዘገብ ወደ አገሪቱ ብዙ ጊዜ ተመላልሻለሁ።ያለ ፍርሃትና ያለማዳላት የጋዜጠኝነትን ሥራ መሥራት መቻል ትልቅ ዋጋ አለው።እኔ የፖለቲካ አክቲቪስት አይደለሁም።አገሬ ናት፤ ንፅሗን ላይ የሚደርሰው ነገር በጣም ያሳስበኛል።ባህላዊና ታሪካዊ ቅርስ ላይ ጥቃት ሲደርስ ልቤን ይሰብረዋል።ነገር ግን ለዚህ ወይም ለዚያኛው አይነት የፖለቲካ አቅጣጫ ቅስቀሳ ማድረግ የእኔ ስራ አይደለም።የእኔ ስራ እየሆነ ያለውን ማንኛውንም ነገር ከተለያየ አቅጣጫ በመመልከት ሸፋን መስጠት ነው።በእርግጥ የኢራንን ህዝብ ሰብአዊነት አጉልቼ ማቅረብ እፈልጋለሁ።እስላማዊው ሪፐብሊክ ሥልጣን ላይ ከተቆናጠጠ ካላፉት 47 ዓመታት ጀምሮ 90 ሚልዪን የሚደርሰው የኢራን ሕዝብ፥ ጨቋኝ እስላማዊ አስተዳደር እንዲሰፍን ፍላጉት እንዳለው አድርጐ ማቅረብ የተለመደ ነው።አብዛኞቹ ኢራናውያን የሚፈልጉት ዲሞክራሲ፣ ኑሮአቸውን ማሻሻልና ልጆቻቸውን በነፃነት ማሳደግ ነው።ትራምፕ አገዛዙን ብቻ ሳይሆን ህዝቡንም በመጨመር አፀያፊ ስድብ እየተሳደበ ነው። ኢራናውያን ዲያብሎሶች ሲል ጠርቷቸዋል፤ የአሜሪካው መከላከያ ሚኒስትር ፒት ሄግሴት ኢራናውያን አረመኔ ሲል ተሳድቧል።

Share this post

Post Comment