የእስራኤልና እና ኤምሬትስ ግንኙነት መጠናከር

የእስራኤልና እና ኤምሬትስ ግንኙነት መጠናከር

እስራኤልና የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች የቆየ የሚባል ወዳጅነት ያላቸው ሀገራት አይደሉም።ከስድስት አመታት በፊት በዶናልድ ትራምፕ ገፉፊነት የአብርሃም ስምምነት ተብሎ የሚታወቀውን ውል ተፈራረሙ።ከዛን ጊዜ ጀምሮ ግንኙነታቸው እየጠነከረ የመጣ ሲሆን በተለይ ግን አሜሪካ እና እስራኤል በኢራን ላይ የከፈቱት ጦርነት ከመቼውም ጊዜ የበለጠ እንዲቀራረቡ አደረጋቸው።ጦርነቱ በእስራኤልና በተባበሩት አረብ ኤምሬቶች መካከል የነበረውን የደህንነት እና ወታደራዊ ዘርፍ ትብብርም በእጅጉ አጠናክሮታል።

የኢራን እስላማዊው አብዮታዊ ዘብ የቀድሞ ከፍተኛ የጦር አዛዥ ሆሴይን ካናኒ ሞግሃዳም፣ “የተባበሩት አረብ ኤምሬትስ ከአሜሪካና ከጽዮናውያን ጋር በማበር በእኛ ላይ ጥቃት እየፈፀመች ነው። የአሜሪካና የጽዮናውያን ወታደራዊ ካምፖች፣ የሚሳይል ማጥቂያ ተቋማት እና የማክሸፊያ ቦታዎች የሚገኙት ኤምሬትስ ላይ ነው።” ብለዋል።

የኢራኑ ጦርነት ከተጀመረ ጀምሮ እንደ ኤምሬትስ ከባድ ዱላ ያረፈበት ሌላ ሀገር የለም።በሰባት ኤምሬትስ የፌዴሬሽን ጥምረት የተመሠረተችው እና የተባበሩት ዓረብ ኤሚሬቶች በመባል የምትታወቀው ሀገር ከ3,300 በላይ የኢራን ሚሳይልና ድሮን ጥቃት ወርዶባታል፤ ይህም በአካባቢው ካሉ አገሮች ላይ ከደረሰው አንፃር ከፍተኛው ነው።በአየር መከላከያ በደንብ የታጠቀችው ኤምሬትስ 96 ፐርሰንት ያህል የሚደርሱ ጥቃቶችን ማክሸፍ የቻለች ሲሆን አስራ ሦስት የሚሆኑ ሰዎች በፍርስራሽ ውስጥ ጉዳት ደርሶባቸው ህይወታቸውን አጥተዋል። ይህ የመከላከል አቅም 11 ሚሊየን ለሚደርሰው ህዝቧ የደህንነት ስሜትን ፈጥሯልሰ። (በነገራችን ላይ፣ 90 በመቶዎቹ የሚሆኑት ነዎሪዎቿ የውጭ ዜጎች ናቸው።)

እንደ ኢራን አተያይ፥ ኤምሬትስ ከአሜሪካ እና እስራኤል ጋር ያበረች፥ የክፉዎች ህብረት (axis of evil) አባል ናት። ከእስራኤል ጋር ያደረገችውን ውል እንደማስረጃ አድርጋ ታቀርበዎለች። “ይሄ የማያሳምን ምክንያት ነው፤ መጀመርያ ነገር የአብርሃም ስምምነት ከተፈፀመ ስድስት አመት አልፎታል።ስምምነቱን ያልፈረመችው ኳታር እንኳ፥ በኢራን በተደጋጋሚ ከመደብደብ አልተረፈችም።” በማለት አንድ የኤምሬትስ ባለሥልጣን ለፈረንሳይ መፅሔት ተናግረዋል። “የተባበሩት ዓረብ ኤሚሬቶች እስራኤልን እንደ ስትራቴጂያዊ አጋሯ ነው የምትመለከታት።ገና አፍላ የሆነው ግንኙነታችን፣ በአጭር ጊዜ ትልቅ እመርታ አሳይቷል፡፡ጦርነቱ ከተጀመረበት ቀን ጀምሮ፣ እስራኤል ከጎናችን ቆማለች።” ብለዋል ባለሥልጣኑ። በወታደራዊ መስክ የሁለቱ አገሮች ግንኙነታቸው እየተጠናከረ ነው።ምክንያቱ ኢራን የጋራ ጠላታቸው ስለሆነች ነው።እስራኤል የኤምሬትስን አየር መከላከያ ሥርዓት የሚያጠናክሩ እና የባልስቲክ ሚሳዔል መከላከያ ጋሻዎችን “አይረን ዶም” ለአቡ ዳቢ ሰጥታለች።ከዚህ ቀደም በጋዛ ጦርነት ወቅት ጥቅም ላይ የዋሉ ሲሆን ከእስራኤል ውጪ ለሌላ ሀገር ሲሰጡ ለመጀመሪያ ጊዜ ነበር።ከዛ በፊት ስፓይደር እና ባራክ የተባሉ ሚሳዔል ማምከኛ መሳሪያዎችን እስራኤል ለኤምሬትስ ሰጥታታለች።

የኔታንያሁ ምሥጢራዊ ጉዞ

ይህ ብቻ አልነበረም። የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ መጋቢት 17 2018 (March 26) ወደ የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች “ምሥጢራዊ ጉዞ” አድርገው ነበር።የቀድሞው የሞሳድ ዳይሬክተር ዴቪድ ባርኒያ፣ የጠቅላይ ኤታ ማዦር ሹም እያል ዛሚር፣ ሺን ቤት የሚባለው የእስራኤል የአገር ውስጥ የደኅንነት መስሪያ ቤት ሹም ሃላፊ ዳቪድ ዚኒ አብረዎቸው ነበሩ።ኔታንያሁ እና ፕሬዝዳንት ሼኽ መሐመድ ቢን ዛይድ መካከል የተደረገው ንግግር “ታሪካዊ እድገት” ማምጣቱን የጠቅላይ ሚኒስትሩ ቢሮ ገልጿል።ይሁን እንጂ ጠቅላይ ሚኒስትሩ እንዲህ ባሉ በአጭር ሰዓት ውስጥ የኤምሬትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር “እውነትን መሠረት ያላደረገ ነው” በሚል ኔታንያሁ አደረግኩት ያሉትን ጉብኝት አስተባብሏል።

በአቡ ዳቢ የእስራኤል አምባሳደር ዮሲ አቭራሃም ሼሊ እንደገለጹት፣ “በመሠረቱ የአብርሃም ስምምነት የኢኮኖሚ ስምምነት ነው።ደግነቱ፣ እስራኤል ጠንካራ እና ታማኝ አጋር አላት።ወዳጃችን በኢራን ያለ ርህራሄ ስትጠቃ፣ ለመርዳት መወሰናችን የሚጠበቅ ነው።የተጠየቅንውን መሣርያ ሁሉ አቅርበንላታል” ሲሉ ለመፅሔቱ ተናግረዋል።

በአቡ ዳቢ የእስራኤል አምባሳደር ዮሲ አቭራሃም ሼሊ

የእስራኤልና የኤሚሬት ጠንካራ ትብብር በኢራን ላይ የተፈፀሙ ጥቃችን ለማካሄድ አስችሏል።ዘ ዎል ስትሪት ጆርናል እንደዘገበው፣ የተባበሩት የአረብ ኤሚሬቶች በኢራን ላይ የወታደራዊ ጥቃት እርምጃዎችን ወስዳለች።እነዚህ እርምጃዎች ከአሜሪካ እና ከእስራኤል ጋር በቅንጅት እንደተፈጸሙ ተገልጿል።የኤሚሬትስ ፖሊሲ ማዕከል ፕሬዚዳንት ኤብቴሳም አል-ኬትቢ እንደገለጹት፣ ዓላማው ኤሚሬትስ ጥቃት የመፈጸም አቅም እንዳላት ለኢራን ማሳየት ነበር።

ይህ ጦርነት በኢኮኖሚው ላይ በተለይ ከባድ ተፅዕኖ በማሳደር፣ ለአቡ ዳቢ ከፍተኛ የኢኮኖሚ መዘዞችን አስከትሏል።የኤምሬትስ ዋና የአክሲዮን ገበያ የሆነው ኤዲኤክስ ጄኔራል በባሕረ ሰላጤ ገበያዎች ከፍተኛውን ኪሳራ አስመዝግቧል።ቱሪዝም እና አቪዬሽን በአየር ክልል መዘጋት እና በስፋት በሚደረጉ የበረራ ስረዛዎች ምክንያት ከፍተኛ ኪሳራ ደርሶባቸዋል። S&P Global የተባለው ድርጅት እንደገለጸው፣ በኤሚሬቶች የቱሪዝም ዘርፍ ከየካቲት 2021 ጀምሮ የቱሪስት መጪዎች ቁጥር ከፍተኛ ቅናሽ በማሳየት በዝቅተኛ ደረጃ ተመዝግቧል።የሆርሙዝ የባሕር ወሽመጥ በመዘጋቱ የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች ዕለታዊ የነዳጅ ምርት ከግማሽ በላይ ቀንሷል።ኤምሬትስ ከ80 በመቶ የሚጠጋውን የምግብ ምርቶችን ከውጭ ሀገራት ስለምታስገባ፣ የዓለም የአቅርቦት ሰንሰለቶች መስተጓገል የምግብ እጥረት ስጋትን ፈጥሯል።

Share this post

Post Comment